




በዞን ደረጃ የተካሄደው የብልጽግና ፓርቲ የአመራር ምዘና መድረክ ከክልሉ አመራሮች ጋር የማጠቃለያ ግምገማ መድረክ በቦንጋ ከተማ ተካሂዷል።
መድረኩ የነበሩ ጥንካሬዎች እና ድክመቶችን ላይ ሰፋ ያለ ግምገማ የተካሄደ ሲሆን መገነባባትንና ውጤትን መሰረት ያደረገ ለብልጽግና ጉዞ ስኬት ከፍ ያለ ተስፋ የሚጣልባቸው ውጤቶች መኖራቸው ተገምግሟል።
በዚህም በአሻጋሪ በብልጽግና እሳቤዎች ቅኝት የአስተሳሰብና የተግባር አንድነትን ለማጎልበት ፣የውሰጠ ፓርቲ አንድነትን ለመፍጠር እንዲሁም የፓርቲና የመንግስት ተግባራትን በትግል በመምራት ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ የተኬደበት ርቀት የሚበረታታ መሆኑን በግምገማው ተነስቷል።
ለፓርቲና ለመንግስት ቅቡልነት መጠናከር መሰረት የሆነውን የጠንካራ ፓርቲ ግንባታ በመገንባት ፣ጠንካራ መንግስትና ሀገረ መንግስት ለመገንባት አበረታች ተግባራት እየተከናወነ መሆኑ በጥልቀት ተገምግሟል።
ጥላቻን፣መጠራጠርንና መነጣጠልን እንዲሁም ዋልታ ረገጥ አስተሳሰብ የሚነዙ ሀሰተኛ ሚዲያዎችን አመራሩ የአስተሳሰብና የተግባር አንድነትን ይበልጥ በማጎልበት በቁርጠኝነት መታገል እንደሚገባ በግምገማው ተዳሷል።
በመፍጠንና በመፍጠር እሳቤዎች በየአካባቢው ያሉትን ሀብትና ፀጋዎችን ወደ ውጤት በመቀየር ለህዝቡ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት መትጋት እንደሚገባ በአጽንኦት ተገምግሟል።
በዚሁ ጊዜ የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን እንደገለጹት የምዘና ስርዓቱ ሁለንተናዊ ብልጽግና የማረጋገጥ ራዕይን እውን ለማድረግ በአስተሳሰብ፣ በስነ ምግባር፣ በእውቀት ፣በክህሎት እና በአፈፃፀም የበቁ እና የላቁ አመራርን ለመፍጠር ቁልፍ ጉዳይ በመሆኑ በቀጣይ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
አመራሩ የፓርቲን ዲስፒሊን በተገቢው መልኩ በመተግበር ሁለንተናዊ የልማት ግቦችን ለማሳካትና የህዝብ ተጠቃሚነትን በላቀ ቁርጠኝነት ለማረጋገጥ መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል ።
የብልጽግና ቤተሰብና የብልጽግና ህብረት አሰራርና አደረጃጀቶችን በማጠናከር የህዝቡን የመልማት፣የመበልጸግና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለማሳለጥ ሁሉም አመራር በተናበበ መልኩ መስራት አለበት ብለዋል።
የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ነጋ አበራ እንዳሉት የፓርቲያችን ኢኒሼቲቦችን የህዝቡን ተጠቃሚነት በተጨባጭ ሊያረጋግጥ በሚያስችል መልኩ በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል።
