






በክልሉ ታርጫ ማዕከል የሚገኙ የብልፅግና ፓርቲ ህብረት አባላት ከቃል እስከ ባህል በሚል መርህ ሃሳብ መነሻ በፓርቲው ሁለተኛ መደበኛ ጉባዔ ውሳኔዎችና በተቀመጠው አቅጣጫ ውይይት አካሂደዋል።
በውይይቱ የተሳተፉ የታርጫ ማዕከል የክልል ተቋማት የብልፅግና ፓርቲ ህብረት አባላት በፓርቲው ሁለተኛ መደበኛ ጉባዔ ውሳኔዎችና በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ተግባራቸውን ለማከናወን ተቀናጅተው እንደሚሠሩም አስረድተዋል።
የታርጫ ማዕከል የክልል ተቋማት የብልፅግና ፓርቲ ህብረት ሰብሳቢ አቶ ማርቆስ ቡልቻ በፓርቲው ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ የተቀመጡ ውሳኔዎች ተግባራዊ እንዲደረጉ የህብረቱ አባላት ሚናቸውን በሚገባ ልወጡ ይገባል ብለዋል።
በውይይታቸው ከቀረበው ሰነድ መነሻ ለተግባር ውጤታማነት ትኩረት ተሰጥቶ ካልተሠራ የኑሮ ውድነትን መቅረፍ እንደማይቻልም ተገልጿል።
ተቋማዊ አቅም ግንባታ በተደራጀ ሁኔታ በማጠናከር ለጠንካራ አገር ግንባታ የድርሻቸውን ለመወጣት በተቀናጀ ርብርብ ተግባራቸውን እንደሚያከናውኑ ተናግረዋል።
አካታች የሆነው ሕብረ ብሔራዊ አንድነትን በማጠናከር ተቋማዊ አንድነትን ከመፍጠር ባለፈ
በክልሉ የተጀመሩ ኢንሼቲቮች ውጤታማ እንዲሆኑ በትኩረት ለመሥራት ተገቢ እንደሆነም ገልጸዋል።
የውጪ ጉዳይ ፖሊሲ ከዚህ ቀደም አጀንዳ ተቀባይ እንጂ አጀንዳ ሰጪ በመሆኑ አገሪቱ የአገር ክብርን ለማስጠበቅ ለሌሎች አገራት ሲሰጥ ከነበረው ካልተገባ ውዳሴም መላቀቅ መቻሉ መልካም ዕድል እንደሆነም ተብራርቷል።
አሁን ላይ በክልሉ የሚገኙ አመራሮች የፖለቲካ ተግባቦት ሥራ በተጠናከረ አኳኋን እያከናወኑ እንደሚገኙም ተገልጿል።
በማዕድን፣ በቡና፣ በቱሪዝምና በሌሎች የገቢ ማስገኛ ምንጮች ላይ በትኩረት በመሥራት ዜጎችን በየደረጃው ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችል ውጤት እንዲመዘገብ የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡም ነው የገለጹት። ደሬቴድ ዋካ ቅርንጫፍ ዘግቧል።
