በግብርናው ዘርፍ የተያዙ ኢኒሼቲቮችን ውጤታማ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የኮንታ ዞን ግብርና አካባቢ ጥበቃና ህብረት ስራ መምሪያ አስታወቀ ።

Spread the love

መምሪያው በግብርና ዘርፍ የልማት ስራዎች የሚያበረታቱ ተግባራት መኖራቸውንም ገልጿል ።

በኮንታ ዞን በግብርና ልማት ስራዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ ተጨባጭ ለውጥ የሚያመጡ ተግባራት እየተከናወኑ ነው።

በዞኑ በተከናወኑ የልማት ስራዎችም የአካባቢው አርሶ አደሮች ከማምረት ባለፈም ምርታቸውን ለገበያ በማቅረብ በኢኮኖሚው ተጠቃሚ መሆን ስለመቻላቸው ተናግረዋል ።

በአመያ ዙሪያ ወረዳ የ01 ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት ወ/ሮ ትዕግስት ከበደ በከተማው በተፈጠረ የሴቶች አደረጃጀት በመታቀፍ የአንድ ቀን ጫጩት በማርባት ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል ።

በዚህም ከዚህ ቀደም የነበረው አደረጃጀት አባላቱ በመበታተናቸው እንደገና በአዲስ በማዋቀር አምስት ሆነው ወደ ስራ ዳግም መግባት ችለናልም ብለዋል።

ወ/ሮ ትዕግስት በአዲስ መልክ ከተደራጁ ወዲህ ለሶስተኛ ጊዜ ጫጬት በመቀበልና አርብተው በመሸጥ ኑሯቸውን ከመምራት ባለፈ የወተት ላሞችን በመግዛትና በመጠቀም፣ በጎችን ገዝተው ለአርቢ በመስጠት በጋራ እየተጠቀሙ መሆኑንና ልጆቻቸውን በማስተማር ከዘርፉ ተጠቃሚነታቸውን አረጋግጠዋል ።

አሁን ላይ ወ/ሮ ትዕግስት በእጃቸው ከአስር ቀናት በኋላ ለገበያ የሚቀርቡ 500 የ45 ቀን ጫጬቶች እንዷላቸውና እነዚህን ከሸጡ በኋላም 500 የአንድ ቀን ጫጩት ለማስገባት በዕቅድ ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል ።

በሰሯቸው የአንድ ቀን ጫጩት ርባታ ስራዎች ከአንድ መቶ ሺህ ብር በላይ ካፒታል እንዳላቸውም በመግለጽ ስራ አጥ የሆኑ ወገኖች ስራን ባለመናቅ ተደራጅተው ወደ ስራ እንዲገቡም መክረዋል ።

ወጣት አንድነት ጌታሁን በከተማው ካሉ የስጋ እና እንቁላል ዶሮ እርባታ ውስጥ የስራ ዕድል ከተፈጠረላቸው አንዱ ነው።

ወጣት አንድነት ዶሮዎችን በመንከባከብ በወር ደመወዝ እየተከፈለው ራሱን ከአልባሌ ቦታ በመጠበቅ ልምድ እያገኘበት ስለመሆኑም ተናግሯል ።

የኮንታ ዞን ግብርናና አካባቢ ጥበቃ ህብረት ስራ መምሪያ ኃላፊ አቶ ማስረሻ አደሮ በሰጡት አስተያየት በዞኑ የበጋ መስኖ ስንዴ፣ የአረንጓዴ አሻራ ና የሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቮችን ውጤታማ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል ።

የመምሪያው ኃላፊ ጨምረው በሰጡት አስተያየት በዞኑ የአረንጓዴ አሻራ አንዱ አካል የሆነው የተፋሰስ ልማት ስራ ባህል ወደ መሆን ተቀይሯል ብለዋል።

በበጋ መስኖ ስንዴም ከዚህ ቀደም ተሞክሮ የማይታወቀው አሁን ላይ ከ154 ሄክታር በላይ መሬት በስንዴ ምርት የተከናወነ መሆኑንም አስረድተዋል ።

በዞኑ በሙዝና አቮካዶ የፍራፍሬ ተክሎች ላይ ትኩረት በመስጠት በተሰራው ስራ አርሶ አደሩ በኢኮኖሚው ተጠቃሚ መሆን የቻለበትና ይህም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ትኩረት በመስጠት ይሰራልም ብለዋል።

በሌማት ትሩፋት ስራዎችም አካባቢው የበለጠ ተጠቃሚ እንዲሆን ለማስቻል ስራ አጦችን በማህበር በማደረጀት በበግና ፍየል ማሞከት፣ በንብ ማነብ እንዲሁም በአንድ ቀን ጫጩትና በወተት ላሞች ርባታ ውጤታማ ስራዎች ተገኝተዋል ብለዋል ኃላፊው።

የዞኑ መንግስት ለዘርፉ በሰጠው ትኩረትም በአመያ ከተማ ሞዴል የዶሮ እርባታ፣ የዓሳ ኩሬ ግንባታና ጫጩት ርባታ ፣ የውጭ ደም ዝርያ ያሏቸውን የወተት ላሞች እርባታ በተከናወኑ ስራዎች ተስፋ ሰጪ ውጤቶች መኖራቸውን አቶ መሸሻ ተናግረዋል ።

በ2017 ግማሽ ዓመት በዞኑ 23 ሸሺህ 814 ቄብና ኮክኔ ለወጣቶችና ለአርቢ አርሶ አደሮች ማሰራጨት ተችሏል ሲሉም አቶ ማስረሻ ተናግረዋል ።

በዞኑ የሌማት ትሩፋት ስራዎች ውጤታማ እንዲሆኑ ለማስቻል የተጀመሩ ስራዎች የሚበረታቱ ሲሆን በተጠናከረ መንገድ መምራት እንዲያስችልም በመንደር አደራጅቶ ለማከናወን በተመረጡ አካባቢዎች 10 መንደሮች በወተት ላሞች ፣ 16 መንደሮች በዶሮ ርባታ ፣ 15 መንደሮች በቀይ ስጋ 7 መንደሮች በንብ ማነብ እና 3 መንደሮች በዓሳ ርባታ መንደሮች ተለይተው እየተሰሩ ይገኛል ብለዋል።

በወተት ላሞችና በዶሮ እርባታ በአመያ ከተማ አስተዳደር እና በጪዳ ከተማ ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ዘመናዊ ሼዶችን በመገንባት የውጭ ደም ያላቸውን የወተት ላሞች እና የአንድ ቀን ጫጬቶችን በማርባት ለማስተማሪያነት እያከናወነ ይገኛል ብለዋል።

በግብርናው ዘርፍ እነዚህንና ሌሎች የክልሉ መንግስት የነደፋቸውን ክልል አቀፍ ኢኒሼቲቮችን በመተግበር ውጤታማ ለማድረግ ከወዲሁ ቁርጠኝነታቸውን አቶ ማስረሻ አስታውቀዋል ።

በታጠቅ አበበ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *