




በክትባት ዘመቻው ከ552 ሺህ በላይ ዕድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች ለሆኑ ህፃናት ተደራሽ እንደሚሆንም ተመላክቷል።
በዕለቱ በታርጫ ከተማ ኢንላይት ህፃናት ትምህርት ቤት የክትባት ዘመቻውን ያስጀመሩት የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ተማም እንደገለፁት ማህበራዊ ብልፅግና ማረጋገጥ የሚቻለው የዜጎችን ጤና በመጠበቅ ሲሆን በሽታን መከላከል የመጀመሪያ ተግባር እና አክሞ የማዳን ደግም ቀጥሎ የሚመጣ ተግባር ነው።
የክትባት ዘመቻ ደግሞ በሽታን ለመከላከል ወሳኝ ተግባር በመሆኑ በሚካሄደው የፖሊዮ ዘመቻ ወላጆች ፣ የአካባቢ ነዋሪዎችና የሚመለከታቸው አካላት ህፃናቱ ክትባት እንዲያገኙ የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።
በሽታው በአንድ ቤት ከተከሰት በአካባቢው ሁሉ ልሰራጭ ስለሚችል በአካባቢው ያሉ ህፃናትን ሁሉ በማስከተብ ወላጆች ሚናቸውን እንዲወጡም አሳስበዋል
የፖሊዮ በሽታን ከሀገራችን ለማጥፋት በሚደረገው ጥረት የመከላከያ ክትባትን ማስከተብና የአካባቢ ፅዳትንም ማጠናከር አስፈላጊ እንደሆነም አቶ ኢብራሂም አመላክተዋል
በክልሉ ክትባት ዘመቻ 552 ሺህ በላይ ዕድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች ህፃናት ተደራሽ እንደሚሆንም አቶ ኢብራሂም አስታውቀዋል፡፡
የዳውሮ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ አስራት ቸርነት መከላከልና አክሞ ማዳን ላይ ትኩረቱን ባደረገው የጤና ፖሊሲያችን የመከላከያ ክትባት ተደራሽ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ ሁሉም የሚመለአተው አካል በጉዳዩ ርብርብ ሊያደርግ ይገባል ብለዋል።
የአካባቢ ፅዳት ተግባራትን በመጠናከር በሽታውን ለማጥፋት ወሳኝ በመሆኑ ልዩ ትኩረት እንደሚሻ በመግለፅ በክትባት ዘመቻው ሁሉም ከ5 ዓመት በታች የሆኑ ህፃናት ተደራሽ እንዲሆኑ የሚመለከታቸው አካላት በቅንጅት ሊሠሩ ይገባል በማለት አሳስበዋል። ደሬቴድ ዋካ ቅርንጫፍ ዘግቧል።
