በኢትዮጵያ የተመረተ አዲስና ዘመናዊ ፓስፖርት ይፋ ሆነ

Spread the love

ዘመኑ የደረሰበትን ቴክኖሎጂ በመጠቀም በኢትዮጵያ የተመረተ አዲስ ፓስፖርት ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በተገኙበት ይፋ ሆነ፡፡

ፕሬዚዳንቱ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር÷ የኤሌክትሮኒክ ፓስፖርትን ተግባራዊ ማድረጋችን የሀገርን ገጽታ ከመገንባት ባሻገር ለዜጎች የተሰጠውን ዋጋ ያሳያል ብለዋል፡፡

ፓስፖርቱ የግለሰቡን መረጃና የጣት ዐሻራ የያዘ የኤሌክትሮኒክስ ቺፕስ አለው ተብሏል፡፡

በኢትዮጵያ ውስጥ የሚመረት ይህ ፓስፖርት፤ የቪዛ ገጾቹ የኢትዮጵያን መልክ የያዙ መሆናቸው ተጠቅሷል።

ይህም ከዚህ ቀደም በውጭ ሀገር አምራች ድርጅት እጅ የነበረውን ዲዛይን ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ መንግሥት እንዲሸፈን አድርጓል ነው የተባለው፡፡

ከዚህ በፊት ይወጣ የነበረውን የውጭ ምንዛሪ በማስቀረት ገቢ ወደ ማመንጨት እንደሚያሸጋግርም ተመላክቷል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *