በእሳት ቃጠሎ በቤት እንስሳትና ንብረትና ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን ፖሊስ አስታወቀ

Spread the love

ህብረተሰቡ ለዘመናት ያፈራውን ሀብት በእሳት እንዳይወድም ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ ፖሊስ አሳስቧል፡፡

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮምሽን የህዝብ ግንኙነትና ኮምንኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ እንደገለፁት የካቲት 13 ቀን 2017 ዓ.ም በአንድ ቀን አራት የእሳት ቃጠሎ መከሰቱንና በንብረትና በቤት እንስሳት ላይ ኩዳት ማድረሱን ተናግረዋል፡፡

የእሳት አደጋው በካፋ ዞን አዲዮ ወረዳ እና ሺሾእንዴ ከተማ አስተዳደር፤በኮንታ ዞን አመያ ዙሪያ ወረዳ በሁለት ቀበሌዎች ሁለት የእሳት አደጋ ማጋጠሙን ያመለከቱት ኢንስፔክተር ደጀኔ ሶስቱ የሳር ኪዳን መኖሪያ ቤቶች ምክንያቱ ባልታወቀ ቃጠሎ ሲደረስባቸው የቃጠሎውን መንስኤ ፖሊስ በማጣራት ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡

በኮንታ ዞን አመያ ዙሪያ በኮዳ ማጅ ቀበሌ የደረሰው ቃጠሎ በባልና ሚስት መካከል በተፈጠረ አለመግባባት ምክንያት ሚስት የሳር ኪዳን መኖሪያ ቤታቸውን በእሳት እንዲያያዝ በማድረጓ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውላ ምርመራ እየተጣራበት እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

በእሳት ቃጠሎው በአንድ ቀን አራት የሳር ኪዳን መኖሪያ ቤት ከነሙሉ ቁሳቁሱ ሲወድም በመኖሪያ ቤት ውስጥ የነበሩ የቤት እንስሳት 2 በሬዎች፤2 ጥጃዎች፤7 ዶሮዎች፤26 ኩንታል ጤፍ፤35 ኩንታል ማሽላ፤2 ኩንታል በቆሎ በእሳት መቃጠላቸውን አስረድተዋል፡፡

እሳቱ በሰው ላይ ጉዳት አለማድረሱን እና እሳቱ ወደ ሌሎች አከባቢዎች ሳይዛመት የመንደሩ ነዋሪዎች ማጥፋታቸውን የገለፁት ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ አሁን ያለንበት ወቅት ደረቅና ነፋሻማ ስለሆነ እሳት እንዲባባስ የሚያደር በመሆኑ እርሻ ማሳ ላይ ለሳር ተብሎ የሚሎኮስ እሳት ሰደድ እሳት ስለሚፈጥር አርሶአደሮች አስፈላጊዉን ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርባቸዋል።

በተመሳሳይ መኖሪያ ቤቶች አከባቢ እሳት እንዳይከሰትና ህብረተሰቡ ለዘመናት ያፈራውን ሀብት ንብረት በእሳት እንዳይወድም ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ አሳስቧል ሲል የደብብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *