በአሶሳ፣ በቦንጋ፣ ሚዛን አማን፣ ደብረ ብርሐን፣ ሻሸመኔና ነቀምቴ ከተሞች ሕዝባዊ ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው

Spread the love

በአሶሳ፣ በቦንጋ፣ ሚዛን አማን፣ ደብረ ብርሐን፣ ሻሸመኔና ነቀምቴ ከተሞች የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፉበት ሀገር አቀፍ ሕዝባዊ ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው።

በከተሞቹ ሕዝባዊ ኮንፈረንስ በብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባዔ የተቀመጡ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች ዙሪያ ሰፊ ውይይት እንደሚደረግ ይጠበቃል።

በኮንፈረንስ የተለያዩ አካባቢዎች የተውጣጡ የህብረተሰቡ ክፍሎች ተሳትፈዋል።

በቤኒሻንጉል ጉሙዝክ ክልል አሶሳ ከተማ በሚካሄደው መድረክ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል እና በብልጽግና ፓርቲ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ኢሳቅ አብዱልቃድር እንዲሁም ሌሎች የክልሉ የአመራር አካላት ተገኝተዋል።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ቦንጋ ከተማ ህዝባዊ ኮንፍረንስ ደግሞ የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አወሉ አብዲ እና የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የጋምቤላ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ጋትሉዋክ ሮን እና ሌሎች አመራሮች ተገኝተዋል።

በዚሁ ክልል ሚዛን አማን ከተማ ህዝባዊ ኮንፈረንስ ደግሞ በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ይርጋ ሲሳይ፣ በብልጽግና ፓርቲ የአፋር ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አቶ መሐመድ አህመድ እንዲሁም የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የመንግስት ረዳት ተጠሪ አቶ በላይ ተሰማ ተገኝተዋል።

በአማራ ክልል ደብረ ብርሃን ከተማ ሕዝባዊ ውይይቱ በብልጽግና ፓርቲ የሲዳማ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ እና በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ከፍያለው ተፈራ ተገኝተዋል።

በሌላ በኩል በኦሮሚያ ክልል ሻሸመኔ ከተማ ሕዝባዊ ኮንፍረንስ የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴ፣ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሯ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ(ዶ/ር) እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።

በዚሁ ክልል ነቀምቴ ከተማ ኮንፈረንስ ደግሞ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር)፣ የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ምክትል ከንቲባ ዣንጥራር ዓባይ እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች እየተሳተፉ ነዉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *