ብልጽግና ፓርቲ ከተመሠረተ በአጭር ዕድሜ ውስጥየህዝብን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ሥራዎችን በማከናወን አስደናቂ ድሎችን አስመዝግቧል፦አቶ አወሉ አብዲ

Spread the love

በቦንጋ ከተማ ሀገር አቀፍ የሕዝብ ኮንፈረንስ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

ውይይቱም ”ከቃል እስከ ባህል” በሚል መሪ ሃሳብ በብልጽግና ፓርቲ 2ኛው መደበኛ ጉባኤ ላይ የተቀመጡ ውሳኔዎች እና አቅጣጫዎች እንዲሁም በመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ዙሪያ ያተኮረ ነው።

በዚሁ ወቅት የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደርና የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አቶ አወሉ አብዲ እንደተናገሩት ብልጽግና በበርካታ ችግር ውስጥ ሆኖ የተወለደ ፓርቲ ነው ብለዋል።

ፓርቲው ከተመሠረተበት በአጭር ጊዜ ውስጥ ያጋጠሙ ችግሮችን በመቋቋም ህብረተሰቡን በማስተባበር የህዝብን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ሥራዎችን በማከናወን አስደናቂ ድሎችን ማስመዝገብ መቻሉንም አቶ አወሉ አብዲ ተናግረዋል።

ፓርቲው በ2ኛ መደበኛ ጉባኤ ያስቀመጣቸው ውሳኔዎች እና አቅጣጫዎች ተፈጻሚ እንዲሆኑ ከህዝቡ ጋር የጋራ በመግባባት በመፍጠር የተጀመረውን የብልጽግና ጉዞ ለማረጋገጥ በሀገሪቱ በትላልቅ ከተሞች የህዝባዊ ኮንፈረንስ መድረክ እያካሄደ ይገኛልም ብለዋል።

ብልጽግና ባለፈው በአንደኛው መደበኛ ጉባኤ ያስቀመጣቸው ውሳኔዎች እና አቅጣጫዎችን ለህዝቡ በገባው ቃል መሠረት በትጋት መፈጸሙንም የገለጹት የጋምቤላ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ዶክተር ጋትሉዋክ ሮን ናቸው።

አሁንም ፓርቲው በሁለተኛው ጉባኤ በቀጣይ ሶስት ዓመታት ለማከናወን ያቀዳቸው ግቦች ከዳር ለማድረስ ከመቼውም ጊዜ በላይ ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራ በመሆኑ ህዝቡ የተለመደውን ትብብር እንዲያጠናክርም ጠይቀዋል።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብሎም ካፋና ቦንጋ ከተማ ምቹ አረንጓዴ ተፈጥሮ ፣ደንና የቡና ምርት ያለበት አከባቢ እንደሆነው ገልጸው እነዚህ እምቅ ሀብቶችን ወደ ተጨባጭ ውጤት ለመቀየር ሁሉም መረባረብ ያስፈልጋልም ብለዋል።

በፍቅር ከበደ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *