



ዩኒቨርሲቲው ለ6ተኛ ዙር በመደበኛና በተከታታይ ትምህርት ፕሮግራም በመጀመሪያ ድግሪ በተለያዩ ትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 2 መቶ 44 ተማሪዎች አመስርቋል።
በትመህርት ዘመኑኑ ወንድ 182 ሴት 62 አጠቃላይ 2መቶ 44 ተማሪዎች ተመርቀዋል።
ተመራቂ ተማሪዎቹ በሀገር ደረጃ የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና ያለፉ ናቸው።
በምረቃው መረሃ ግብረ የተገኙት የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጉቼ ጉሌ እንደገለፁት ዩኒቨርስቲው መንግሥት ለትምህርት ጥራትና ተደራሽነት የሰጠውን ትኩረት በመቀበል ብቁ እና ተወዳዳሪ ዜጋ ለማፍራት እየሰራ ይገኛል
በካምፓሱ በትምህርት መስኮችና በመሠረት ልማት ዘርፍ አመርቂ ተግባራት የተከናወኑ ቢሆንም ገና ረጅም ርቀት ያለ በመሆኑ የአከባቢውን የተፈጥሮ ፀጋ በመለየት በትኩረት ልሰራ እንደምገባ ነው ያብራሩት።
የወላይታ ሶዶ ዩንቨርስቲ ዳውሮ ታርጫ ካምፓስ ዲን ተባባሪ ፕሮፌሰር መብራቱ ለገሰ በበኩላቸው ካምፓሱ ለተከታታይ አስር ዓመታት ጥራት ያለውን ትምህርትና ችግር ፈቺ የሆኑ ምርምሮችን ሲያከናውን ቆይቷል ብለዋል።
ግብርና፣ ከርሰ-ምድር ጥናት፣ሥነ-ሰብና ኢንጂነርንግ ቴክኖሎጂ የካምፓሱ የትኩረት መስኮች መሆናቸውን ገልፀዋል።
ተ/ፕ መብራቱ መላው ተመራቂ ተማሪዎች የላቀ አስተዋጽኦ ያበረከቱትን ማህበረሰቦችን በብቃትና በትህትና እንድያገለግሉ አሳስበዋል።
ተመራቂዎቹ ሥራ ፈጣሪ ብቻም ሳይሆኑ ተወዳዳሪ፣ ተስፋ እና ራዕይ ያላት ኢትዮጵያን ለማፍራት ሊረባረቡ እንደሚገባ የገለጹት የዳውሮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ገበየሁ ናቸው።
በ2017 ትምህርት ዘመን ከተመረቁ ተማሪዎች መካከል በትምህርታቸው ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ለወንድና ሴት ተማርዎች የሜዳልያ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
በምረቃ ሰነ ሰርዓት የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጉቼ ጉሌ፣ ምክትል ፕሬዚዳንቶች፣ የዳውሮ ታርጫ ካምፓስ ዲን ተ/ፕ መብራቱ ለገሰ፣ የዩኒቨርስቲው እና የካምፓሱ አመራር አባላት፣ የዳውሮ ዞን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች የሀይማኖት አባቶች እንዲሁም ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተውበታል ሲል የዳውሮ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።
