





የደቡብ ምዕራብ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ኮርፖሬሽን የ2017 ዓ.ም የግማሽ ዓመት አፈፃፀም ከስራ አመራር ቦርድ ጋር በቦንጋ ከተማ ገምግሟል፡፡
ኮርፖሬሽኑ በግማሽ ዓመቱ በክልሉ በ10 ከተሞች በሚሰሩ 11 የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች የጥናትና ዲዛይን እንዲሁም ግንባታ ቁጥጥር ስራዎች በመስራት የተሻለ አፈፃፀም ማስመዝገብ የተቻለ መሆኑ በቀረበው ሪፖርት ተመልክቷል፡፡
የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በመስኖና በንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች የግንባታ ጥናት ዲዛይንና እና ቁጥጥር በ6 ወር ውስጥ የተሻለ አፈፃፀም የተከናወነ መሆኑን አንስተው ኮርፖሬሽኑ ከህንፃ፣ ከመንገድና ከድልድይ ግንባታ ፕሮጀክቶች አካባቢ ያለው የአፈፃፀም ውስንነቶችን በማረም በቀጣይ ውጤታማ ለመሆን ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
ኮርፖሬሽኑ አትራፊ የመንግሥት የልማት ድርጅት በመሆኑ የውስጥ ገቢ አቅም በማሳደግ ላይ ትኩራት ሰጥቶ መስራ እንዳለበት ጠቅሰው ለዚህም ጥራትና ብቃት ያለው የሰው ሃይል አደረጃጀትን ማጠንከር አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የደቡብ ምዕራብ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ኮርፖሬሽን ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ፍቅሩ ለዊ፤ በክልሉ ያለውን የመሠረተ ልማት ክፍታቶች በጥናትና ዲዛይን ለመደገፍ ኮርፖሬሽኑ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ኮርፖሬሽኑ ገበያ ላይ ተወዳዳሪ ሆኖ ከመቆየት ባለፈ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ስራዎችን በጥረት ደረጀ ሰርቶ ለማስረከብ በተሻ ሁኔታ የሚሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የኮርፖሬሽኑ ስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ኢንጂነር የማታለም ቸኮል በበኩላቸው የክልሉ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ኮርፖሬሽን ስራዎችን በተፈለገው ጊዜ አጠናቆ ለማስረከብ ያለውን የሰው ሃይል በተገቢው መጠቀምና ስራዎችን በፍጥነት እና በጥራት መስራት ይጠበቃል ብለዋል፡፡
ለዚህም ተቋሙ የራሱን አቅም በመወቅ የውስጥ ገቢውን በማሳደግ፤ የበጀት አቅምን ታሳቢ ያደረገ ወጪ መንገድ መከተል አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል፡፡
በክልሉ የመሠረተ ልማት ስራዎችን ለማሟላት በሚደረገው ሂደት ላይ ፕሮጀክቶች ወጪ ቆጣቢ፣ ጥራታቸው የተጠበቁና በወቅቱ አገልግሎት ፈላጊ ማህበረሰብ ተደራሽ በማድረግ የራሱን ድርሻ ሊወጣ እንደሚገባም ኢንጂነር የማታለም አሳስበዋል፡፡
በመድረኩ የኮርፖሬሽኑ የ2017 ዓ.ም የግማሽ ዓመት የአፈፃፀም የተገመገመ ሲሆን ለኮርፖሬሽኑ ነባር ሠራተኞችና ኃላፊዎች በአዲሱን ደመወዝ ላይ ተወያይቶ በመወሰንና የአሰራር መመሪያ በቀጣይ መርምሮ ለማፅደቅ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ተጠናቋል፡፡
በተከተል ወ/ሚካኤል
