በብልፅግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ የተላለፉ ውሳኔዎችና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች በመፈፀም የሀገሪቱን ሁለንተናዊ ብልፅግና ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገለፀ።

Spread the love

በምዕራብ ኦሞ ዞን በጀሙ ከተማ “ከቃል እስከ ባህል!” በሚል መሪ ቃል በተካሄደው 2ኛው የብልፅግና ፓርቲ መደበኛ ጉባኤ ወሳኔ እና አቅጣጫዎች ላይ ከከተማ ማህበረሰብ ጋር ዉይይት እየተደረገ ይገኛል።

በመድረኩ የክልሉ የአካባቢው እና ደን ጥበቃ ቢሮ ሃላፊ ዶክተር አስራት ገብረማርያም እንደተናገሩት ብልጽግና ፓርታ በባለፉት አመታት በርካታ ሥራዎች ሰርቷል ብልዋል።

ዶክተር አስራት በ2ኛው የብልፅግና ፓርቲ መደበኛ ጉባኤ ላይ የተላለፉ ውሳኔዎች ፣የጠንካራ ፓርቲ ግንባታን ማጠናከር ፣ ብሔራዊነትና ገዢ ትርክት ግንባታን ፣ ውጤታማ የሰላም ግንባታ፣

የፍትህ ዘርፍ ውጤታማነትን ማሳደግ ፣ ሀገረ መንግስት ግንባታ ፤የኢኮኖሚ ልማትን ማፋጠን ፣ ማህበራዊ ብልፅግናን ማረጋገጥ ፣ ውጤታማ ዲፕሎማሲያዊ ስራዎችን መስራት

፣ የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ውጤታማነትን ማረጋገጥ ፣ ጠንካራ የሚዲያና ኮሚኒኬሽን ሥራ መስራት እንዲሁም የቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ በሰነድ በዝርዝር እያቀረቡ ይገኛል።

ከለውጡ ማግስት የተሰሩ ስራዎችን እንደ መነሻ እርሾ በመጠቀም በቀጣይ የሀገሪቱን ሁለንተናዊ እድገት ብልፅግና ማረጋገጥ እንደሚገባ ዶክተር አስራት ተናግረዋል።

የዞኑ ዋና አስተዳደሪ አቶ ጌታቸዉ ኬኒ እንደተናገሩት በከተማው የተጀመሩት ሥራዎች ተጠናክሮ እንዲቀጥል የከተማ የማህረሰብ ሃላፊነታቸውን መወጣት እንዳለባቸው ገልጸዋል።

የሀገሪቱን ብልፅግና ዕውን ለማድረግ በቀጣይ አመታት ማህበረሰቡ የስራ ባህልን ማዳበርና ህብረ-ብሔራዊ አንድነትና ገዢ አሰባሳቢ ትርክትን ማጠናከር እንደሚገባ ተናግሯል።

በ2ኛው የብልፅግና ፓርቲ መደበኛ ጉባኤ የተላለፉ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎችን ተፈፃሚነታቸውን ለማረጋገጥ ሁሉም የበኩላቸውን ሚና እንደሚወጡ አስገንዝበዋል።

በመድረኩ የጀሙ አተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አሸናፊ ተስፋዬ በባለፉት አመታት የተከናወኑ ተግባራትና የተገኙ ዉጤቶች የሚገልፅ ሰነድ አቅርቧል።

በሰነዱ በኢኮኖሚና በማህበራዊ ዘርፎች የተሰሩ ስራዎች ፣ በመልካም አስተዳደር ተለይተው የተፈቱ ጉዳዮች ፣ የመሬት ዝግጅት ፣ አቅርቦት በተመለከተ ፣ የአገልግሎት አሰጣጥ እንዲሁም ከዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ጋር ተያይዞ የተሰሩ ዋና ዋና ተግባራትን በዝርዝር አቅርበዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *