



በክልሉ ከሽካ ዞን በስተቀር በአምስት ዞኖች ስፋቱና የጉዳቱ መጠን የተለያየ የደን እሳት ቃጠሎ መከሰቱን አስታውቀዋል።
በካፋ ዞን በጠሎ እና በአዲዮ ወረዳዎች አዋሳኝ አካባቢ ደን ላይና በዴቻ ወረዳ ዳኪቲ ቀበሌ እንዲሁም በገዋታ ወረዳ የደን ቃጠሎ ተከስቶ ማህበረሰቡን በማስተባበር ለመቆጣጠር እየተሠራ ነው ብለዋል።
በዳውሮ ዞን ማረቃ አደአ፣ ማሪ ወረዳ፣ ታርጫ ዙሪያ ወረዳ እና ሎማ ወረዳ የእሳት ቃጠሎ የተከሰተ ሲሆን ፤ ማስቆም መቻሉን ዶክተር ኢንጂነር አስራት በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል።
በተመሣሣይ ሁኔታ ምዕራብ ኦሞ ዞን ሱርማ፣ ጋቺትና ሜኤኒት ሻሻ ቃጠሎ መከሰቱን ገልጸው ፤ በቤንች ሸኮ ዞን ተጨማሪ መረጃ የማጣራት ሥራ በሂደት ላይ ነው ብለዋል።
በሌላ በኩል በኮንታ ዞን ጨበራ ጩርጩራ ፓርክ አካባቢ ተከስቶ የነበረውን የእሳት አደጋ መቆጣጠር መቻሉን እና በዚያው አካባቢ ጎራ በተሰኘ ቀበሌ በሰብል ላይ ውድመት መከሰቱን ነው ያመላከቱት።
የቃጠሎ መነሻ ምክንያቶች ህገ-ወጥ የከሰል ምርት እና ጥንቃቄ የጎደለው ቆሻሻ ማቃጠል መሆኑ መረጋገጡን ጠቁመዋል።
በመሆኑም ማህበረሰቡ በተፈጥሮ ሀብት፣ በሰው ህይወት እና በንብረት ላይ የከፋ አደጋ እንዳይከሰት ጥንቃቄ እንዲያደርግ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የአደጋ ምልክት ሲታይ በአስቸኳይ ጥቆማ እንዲሰጥ ጠይቀዋል።
ለአደጋው ምክንያት የሆኑ አካላትን በተገቢው በማጣራት ለህግ የማቅረብ ሥራ እየተሰራ መሆኑን ዶክተር ኢንጂነር አስራት አስታውቀዋል።
