ከሸቀጦች የወጪ ንግድ ከ3 ነጥብ 84 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ

Spread the love

ባለፉት ሰባት ወራት ከሸቀጦች የወጪ ንግድ ከ3 ነጥብ 84 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገለጹ።

ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ በሸቀጦች የወጪ ንግድ የእቅዱን 146 በመቶ መፈጸም መቻሉን አመልክተዋል።

ለገቢው መገኘት ወርቅ፣ ቡና፣ የቅባት እህሎች፣ ኤሌክትሪክ እና የቁም እንስሳት ወጪ ንግድ ከእቅዳቸው በላይ ማስገኘት የቻሉ የወጪ ንግድ ምርቶች ናቸው ብለዋል።

ባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ከተገኘው የ1 ነጥብ 9 ቢሊየን ዶላር ገቢ ጋር ሲነፃፀር የ1 ነጥብ 94 ቢሊየን ዶላር ወይም የ101 ነጥብ 2 በመቶ ብልጫ እንዳለው ገልጸዋል።

አፈፃፀሙ ይበልጥ እንዲጠናከር ጥብቅ ድጋፍና ክትትል የሚደረግ ይሆናል ሲሉ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል ሲል ኤፍ ኤም ሲ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *