129ኛው የአድዋ ድል መታሰቢያ ምክንያት በማድረግ በቦንጋ ከተማ በአካላዊ እንቅስቃሴና ፅዳት ዘመቻ ተካሄደ።

Spread the love

በመርሀ-ግብሩ መልዕክት ያስተላለፉት፥ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ ኢንጅነር የማታለም ቸኮል በአድዋ አባቶቻችን ያስመዘገቡትን ድል የአሁኑ ትውልድ በልማት መስክ መድገም አለበት ብለዋል።

ከተሞች ለኑሮ ምቹ እንዲሆኑ ዘወትር በየሣምንቱ የፅዳት ዘመቻ ማድረግን ህብረተሰቡ ባህል ማድረግ እንደሚገባ ያስገነዘቡት ኢንጅነር የማታለም ንቁ ዜጋ ለልማት ወሳኝ በመሆኑ ስፓርቲዊ እንቅስቃሴ ማዘውተር ይገባል ብሏል።

የቦንጋ ከተማ ከንቲባ አቶ አስማማው አደመ በበኩላቸው ከተሞች ለነዋሪዎች ምቹ እንዲሆኑ የተጀመረው የጽዳት ዘመቻ በየሣምንቱ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።

አባቶቻችን በአድዋ በወራሪው ሀይል የተቀዳጁትን ድል የዛሬው ትውልድ በልማት እና በፀረ ደህነት ትግል ላይ መቀዳጀት እንደሚገባ የገለጹት ካንቲባ አስማማው አሁን ላይ የሚገጥሙንን ፈተናዎች ሁሉ የአድዋ መንፈስ በመላበስ ማሸነፍ እንደሚገባ ተናግረዋል።

በመርሀ-ግብሩ ከተገኙት መካከል ‘የአብ ጅም’ አባል አቶ ታዬ ታከለ እንደገለጹት፥ አባቶቻችን በቁርጠኝነት በውጭ ወራሪ ሀይል ላይ ያገኙት ድል የዛሬው ትውልድ ጤንነቱን በተገቢው በመጠበቅ በተሰማራበት መስክ ሁሉ ውጤታማ በመሆን መድገም አለበት ብሏ።

ስፓርቲዊ እንቅስቃሴ በማዘዋወር ከተላላፊ በሽታዎች ራሰን በመከላከል ውጤታማ ዜጋ መሆን እንደሚገባ የገለጸው አቶ ታዬ የአድዋ በዓል መታሰቢያን ምክንያት በማድረግ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ በከተማው መደረጉ የሚበረታታ ተግባር መሆኑን ተናግረዋል።

በመርሀ-ግብሩ የከተማው የህብረተሰብ ክፍሎች የክልሉ፣ የከፋ ዞን እና የቦንጋ ከተማ ነዋሪዎች እና ስፖርተኞች የተገኙት ሲሆን ስፖርታዊ እንቅስቃሴ እና የፅዳት ዘመቻ ተካሂዷል።

በዕድገቱ በዛብህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *