በክልሉ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ አዘጋጅነት እየተካሄደ ያለው የስነ ጥበብና ኪነ ጥበብ ዉድድር በህሩት ምትኩ አሸናፊነት ተጠናቋል።

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ያዘጋጀው ክልላዊ የኪነ- ጥበብ እና ስነ-ጥበብ ፈጠራ ውድድርና ትዕይንት በዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ ተካሂዷል።

የክልሉ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ባዘጋጀዉ ክልላዊ የስነ ጥበብና ኪነ ጥበብ ዉድድር ሚስ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በመሆን ከቤንች ሼኮ ዞን ህሩት ምትኩ አሸንፋለች፡፡

በተመሳሳይ መልኩ በስዕል ዉድድር የከፋ ዞን ወክሎ የቀረበዉ ሰዓሊ አብረሃም ተስፋዬ አሸናፊ የሆነ ሲሆኖ

በፍልሙም ብቸኛው ተወዳዳሪ በመሆን ከፋ ዞን ወክሎ ተገኝ አስጋሄኝ በአድነት አጠናቀዋል።

በውዝዋዜ ውድድር እልፍነሽ ኢትዮጵያ ዳውሮ ዞን በመወከል ያሸነፈ ሲሆን በስነ ጽሑፍ ውድድር ቤንች ሼኮ ዞን በመወከል ናኦድ ውበቱ የአድነት ደረጃ የወጣ ሲሆን በፎቶ ግራፍክስ ቤንች ሼኮ ዞን በመወከል ምንተስኖት ከበደ አንደኛ ወጥተዋል።

ውድድሩ በሞዴሊንግ፣ በፋሽን ዲዛይን፣ፍልም፣ውዝዋዜ እና በስዕል ውድድር በሁሉም ዞኖች መካከል ልዩ ፉክክር የተደረገ ሲሆን ዞኖችን ለወከሉ ተወዳዳሪዎች የእውቅና ሠርተፍከት ተበርክቶላቸዋል።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ፋንታሁን ብላቴ ኪነ-ጥበብ ውድድር በክልሉ ያለውን እምቅ ዕውቀትን ያወጣ ሲሆን ይህንኑን ለኢኮኖሚያዊ ሽግግር በመጠቀም ክልሉን በዘርፉ ማስተዋወቅ እንደምገባ ገልፀዋል።

አቶ ፍንታሁን ኪነ-ጥበብ ውድድር የተሳተፉትን የመሩትን በማመስገን ቀጣይ በሀገር ደረጃ ለምደረገው ውድድር ክልላችን የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ መቻል አለብን ስሉ በማሳሰብ ውድድሩን አጠቃለዋል።

በአጠቃላይ በክልላችን በዚህ ዘርፍ አቅም ያላቸወን አካላት በማወዳደርና ዕውቅና በመስጠት በፌዴራል ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆን የሚያስችል ሥራ እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል። ዘገባው የዳውሮ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *