የድጋፍና የሱፐርቪዥን ስራዎች በክልሉ ባሉት የአስተዳድር እርከኖች ቋሚ ባህል እስኪሆን ድረስ አበክረን መደገፍና መስራት ይገባል፦ አቶ ፍቅሬ አማን

Spread the love

በክልሉ እየተከናወኑ ያሉ የፓርቲና የመንግስት ስራዎች ያለበት ደረጃ በተጨባጭ ወርዶ ለማረጋገጥና ለመደገፍ የማስፈጸሚያ ዕቅድ መድረክ በቦንጋ ከተማ ተካሂዷል።

የድጋፋዊ ሱፐርቭዥን ዋና አላማ በክልሉ እየተከናወኑ ያሉ የፓርቲና የመንግስት ስራዎችን መድረክ ላይ ከመገምገም ባለፈ መሬት ላይ ያለበትን ደረጃ ምልከታ በማድረግ ጥንካሬና ጉድለቶችን በመለየት ፣ጉድለቶች ታርመው የአፈጻ ም ብቃትና ጥራት እንዲረጋገጥ ለማስቻል ነው።

የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን ለክልሉ አመራሮች ቀጣይ ለሚካሄደው ድጋፋዊ የሱፐርቪዥን ቡድን ስምሪት ላይ እንደገለጹት የተደራጀ፣ የተናበበና ቀጣይነት ያለዉን የድጋፍ፣ክትትልና የግምገማ ስርዓት በመዘርጋት የአስተሳሰብ፣ የተግባርና የአሰራር ሂደትንና ወጤትን በመመዘን ክፍተቶች እንዲታረሙና መልካም ስራዎች ተጠናክሮ እንዲቀጥሉ በማድረግ የጠንካራ ፓርቲ ግንባታ ስራንና የመንግስት የመፈጸምና የማስፈጸም አቅምን ማጠናከር ይገባል፡፡

በፓርቲ እና በመንግስት የተቀመጡ ግቦችን ከዳር ለማድረስና ውጤታማነትን ለማረጋገጥ ድጋፋዊ የሱፐርቪዥን ስራዎች ሚናው የጎላ እንደሆነ ገልጸዋል።

የድጋፋዊ ክትትልና ሱፐርቭዥን ስራዉ በጥብቅ ድስፒልን የሚመራ፣ ተግባራትን ወደፈፃሚዉና ታችኛዉ አደረጃጀት ድረስ ወርዶ በመመልከት፣ ጥንካሬና ጉድለትን በተጨባጭ መለየት ይገባል ብለዋል።

ማብቃትን ማዕከል ያደረገ ግብረ መልስ በየደረጃዉ በመስጠት በክልሉ ለማሳካት የታለመውን የወጤት ልህቀት ለማረጋገጥ በተናበበ መልኩ መስራት ይጠበቃል ብለዋል።

የፖለቲካና ስራዎች ከላይ እስከ ታች በተቀናጀና በተናበበ መልኩ ተግባራትን በቁርጠኝነት በመፈጸምና በማስፈጸም ይገባል ያሉት አቶ ፍቅሬ በአደረጃጀቶች አሠራር ስርዓት መሰረት የብልጽግና ቤተሰብና የብልጽግና ህብረት በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ትኩረት አድርጎ ውይይት ማድረግ ይገባል ብለዋል።

የህዝቡን ተጠቃሚነት ሊያረጋግጡ የሚያስችሉ በፓርቲያችን የተጀመሩት ኢኒሼቲቦችን አጠናክሮ ለማስቀጠል የሚያስችል አስቻይ ሁኔታዎችን በመለየት የሱፐርቪዥን ቡድን አባላት ትኩረት አድርጎ መስራት እንዳለበት ገልጸዋል።

በዚህም በክልሉ ባሉት ዞኖች ወረዳዎች ከተማ አስተዳደሮች ና በቀበሌዎች ደረጃ ቋሚ ባህል እስኪሆን ድረስ አበክረን መደገፍና መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል ።

የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ነጋ አበራ እንዳሉት የተቀናጀ ድጋፋዊ ክትትል በማድረግ በሁሉም ዘርፍ ውጤታማ የተግባር አፈጻጸም ለማስመዝገብ አመራሩ በትኩረት መስራት እንዳለበት ገልጸዋል።

ድጋፋዊ የሱፐርቪዥን ከስኬት ከመቀመርና ጉድለቶችን ከመማርና በተጨማሪ የተሻሉ አቅሞችን ወደ ታች ለማውረድ የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል።

የክልሉ ምክትል ርዕሰ መርተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው የገጠር ኮሪደር ልማት መተግበሪያ ዕቅድ ባቀረቡት ሰነድ አቅርበዋል።

የገጠር ኮሪደር ልማት በገጠር አካባቢዎች የኢኮኖሚና የልማት ዕድገትን ለማሳደግ የሚከናወን ተግባራተ ማዕቀፍ በመሆኑን አመራሩ ለዕቅዱን ተግባራዊነት ተግቶ መስራት እንዳለበት ገልጸዋል።

በዚህም የአርሶና አርብቶ አደሩን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ መስተጋብር ለመሳደግ በተናበበ መልኩ መስራት አለብን ብለዋል።

በክልሉ ያሉትን ምቹ ሁኔታዎችን በመጠቀም የተጀመረውን የብልጽግና ህልሞችን ለማሳከት የተቀናጀ ርብርብ ማድረግ ይጠበቃል ብለዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *