
ዓለም ዓቀፍ የሸማቾች ቀን “ጥራቱ የተጠበቀ ምርት ለሸማቾች” በሚል መር ሃሳብ በአዲስ አበባ እየተከበረ ነው።
በዓለም ለ42ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ12ኛ ጊዜ በሚከበረው የዓለም የሸማቾች ቀን የፌዴራልና የአዲስ አበባ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ሀላፊዎች፣ ሸማቾች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ኃላፊ ሀቢባ ሲራጅ በዚሁ ወቅት ከተማ አስተዳደሩ ሸማቹ ማህበረሰብ በተመጣጣኝ ዋጋ ጥራት ያለው ምርት እንዲያገኝና ጊዜ ካለፈባቸው ምርቶች እንዲጠበቅ ለማድረግ በርካታ ሥራዎች ተከናውነዋል፡፡
በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የሀገር ውስጥ ንግድና ሸማቾች ጥበቃ መሪ ስራ አስፈጻሚ ሊቁ በነበሩ በበኩላቸው እንደገለጹት የምርት ጥራት እና አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የጥራት መንደር ወደ ስራ ገብቷል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡
