በህዝብ ዘንድ የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች አድምጦ ፈጣን ምላሽ በመሰጠት ለህዝበ ተጠቃሚነት በቁርጠኝነት መስራት ይገባል ፦አቶ ፍቅሬ አማን

Spread the love

በህዝብ ዘንድ የሚነሱ የመልካም አስተዳድር ጥያቄዎች አድምጦ ፈጣን ምላሽ በመሰጠት ለህዝበ ተጠቃሚነት በቁርጠኝተን መስራት እንደሚገባ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን ገለጹ

የመልካም አስተዳድር ችግሮችን ማዕከል ያደረገ

ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ የውይይት መድረክ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን እንደገለጹት በአገልግሎት አስጣጥ ላይ የህዝቡ ጥያቄዎችን አድምጦ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት በቁርጠኝነት በማገልገል የህዝቡን እርካታ ማሳደግ ይገባል ብለዋል።

በአገልግሎት አሰጣጥ ሂደት ፍትሀዊ ፣ቀልጣፋና ውጤታማ እንዲሆን አመራሩ ከምን ጊዜውም በላይ መስራት እንዳለበት አጽኖት ሰጥተዋል።

ተቋሙን የሚመራው አመራር ከፓርቲና ከመንግሥት የተጣለበትን ኃላፊነት በሙሉ አቅም በመወጣት የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን የመፍታት፣በፍትህ ስርዓት የሚስተዋሉ ጉድለቶችን ማረም እና ሌብነትና ብልሹ አሰራርን የመታገል ተግባራት በቅንጅት እንዲፈጸሙ አሳስበዋል።

በቀጣይ የተቀዱ ዕቅዶችን በመከለስ በመልካም አስተዳድር ችግሮች በማሳለጥ እመርታ ለማስመዝገብ የተቀናጀ ርብር ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል

በመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ዙሪያ እስካሁን የተከናወኑ አንካር ጉዳዮች ሪፖርት እየቀረበ ሲሆን ቀጣይ ልዩ የትኩረት አቅጣጫ እንደሚቀመጥ ተገልጿል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *