በክልሉ የተገነቡ የመስኖ አውታሮችን በመጠቀም በበጋ መስኖ ስንዴ እና በሌሎች አትክልትና ፍራፍሬ ልማት ሥራዎች ለውጥ እያመጡ በመሆኑ ተጠናክሮ ይቀጥላሉ፦ ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር)

Spread the love

በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ የተመራ የከፍተኛ አመራሮች በካፋ ዞን ጨና ወረዳ በቀነች እና ኦፊያ አነስተኛ መስኖ በክላስተር የለማ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ያለበትን ደረጃ ተመለከቱ።

በወረዳው በቀነች እና ኦፊያ አነስተኛ መስኖ በክላስተር 1 እና 2 በ86 ሄክታር መሬት የለማ የበጋ መስኖ ስንዴ እና በ192 ሄክታር መሬት የለማ የሽንኩርትና ሌሎች የፍራፍሬ ምርቶችን አመራሮች ተዘዋውረው ተመልክቷል።

በጉብኝቱ ወቅት ርዕሰ መስተደድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) እንዳሉት፤ የግብርና ምርትና ምርታማነት በማሳደግ የምግብ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ ባለፉት ጥቅት ዓመታት በጀመርንባቸው ሥራዎች ሰፊ ለውጦች እየታዩ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ያለውን የተፈጥሮ ሀብት በመጠቀም መሬትና የውሃ አማራጮች በማልማት የግብርና ምርትና ምርታማነት በማሳደግ በቤተሰብ ደረጃ እና የሀገር ውስጥ የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ እየተሰራ ይገኛል ።

ከዚህም ባሻገርም ወደ ዉጪ የሚላኩ የግብርና ምርቶችን በስፋት በማምረት የውጪ ምንዛሬ ለማሳደግ እና በሀገር ውስጥ ለአግሮ ኢንዱስትሪ የሚቀርቡ ምርቶችን በስፋት ማምረት ትኩረት የተሰጠባቸው ጉዳዮች እንደሆናቸውም ርዕሰ መስተዳድሩ አስረድተዋል።

በዚህም ከውጪ የሚገባውን የስንዴ ምርት ለማስቀረትና ከውጭ የሚገባውን ምርት በሀገር ውስጥ ለመተካት በተደረጉ መጠነ ሰፊ ሥራዎች ለውጦች እየተመዘገቡ መሆናቸውን ነው ዶክተር እንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ የጠቆሙት።

ርዕሰ መስተዳድሩ በካፋ ዞን ጨና ወረዳ ሁለት አነስተኛ የመስኖ ፕሮጀክት ግንባታዎች ተገንብተው ወደ ሥራ በመግባቱ አርሶ አደሮቹ ይህ የመስኖ ልማትን በመጠቀም በ86 ሄክታር መሬት የበጋ መስኖ ስንዴ እና የተለያዩ የፍራፍሬ ምርቶች እና አትክልቶችን እየለሙ የሚገኙ ሥራዎች የሚበረታታ መሆኑን በመስክ ምልከታ ወቅት ማረጋገጥ ችለናል ነውያሉት ።

ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ በሌሎች አከባቢዎችም 7 ዘመናዊ አነስተኛ የመስኖ ፕሮጀክት ግንባታዎች ተገንብተው ወደ ሥራ ገብቷል ያሉት ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ በዚህም የበጋ መስኖ ስንዴና በሌሎች ምርቶች የተጀመሩ ሙከራዎች እየመጡ ያሉ ለውጦች እንደሚጠናከሩም በንግግራቸው ጠቁመዋል።

በክልሉ በዘንድሮ ዓመት በ2ኛ ዙር መስኖና በበልግ 103 ሺህ ሄክታር ማሳ በማልማት ወደ 27 ሚሊዮን ኩንታል ምርት እንደሚጠበቅ የክልሉ ምክትል ርዕሰመሠተዳደርና ግብርና ቢሮ ሀላፊ አቶ ማስረሻ በላቸዉ ተናግረዋል።

5 ሺህ 50 ሄክታር ማሳ በበጋ መስኖ ስንዴ መልማቱን ጠቁመዉ ምርታማነቱንም በሄክታር ከ38 ኩንታል በላይ ለማድረስ መታቀዱንም ጠቁመዋል።

ባለፉት ዓመታት በክልሉ የመስኖ አዉታሮችን ለማስፋት በተሰራዉ ስራ ዉጤት መታየቱን ገልፀዉ፣ ባለፈዉ ሀምሌ ወር ላይ የተመረቁትን የቄነችና ኦፍያ አዉታሮችን በመጠቀም እየለማ ያለዉ የበጋ መስኖ ስንዴና አትክልት ለሌሎችም አርአያ የሚሆን ነዉ ብለዋል።

በክልሉ መደበኛ የዝናብ ወቅት ከመጠበቅ ባሻገር በተገነባው የመስኖ አውታሮች እየተሰሩ ያሉ የበጋ መስኖ ስንዴ እና ሌሎች የግብርና ምርቶች ምርትና ምርታማነት በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እየተሰራ ያለው ስራ ለውጥ እያመጣ በመሆኑ ዛሬ በጉብኝቱ የተመለክትነው ሥራዎች ማሳያ እንደሆናቸውም የገለጹት የክልሉ የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ፍቅሬ አማን ናቸው።

የካፋ ዞን ዋና አስተዳደሪ አቶ እንዳሻው ከበደ በበኩላቸው በክልሉ መንግስት በተገነቡ የመስኖ አውታሮች በመጠቀም አርሶ አደሮች በካፋ ዞን ጨና ወረዳ እየሰሩ ያሉ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማትና ሌሎች ግብርና ሥራዎች የሚበረታቱ በመሆኑ ቀጤይነት እንዲኖረው የድጋፍ ሥራዎች ይጠናከራሉ ብለዋለል።

በጉብኝቱ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ፣ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ፍቅሬ አማን፣ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው፣ ጨምሮ የክልል፣ የካፋ ዞንና የጨና ወረዳ ከፍተኛ አመራሮችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳትፈዋል።

በፍቅር ከበደ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *