በዞኑ በገጠርና በከተማ ለኢንቨስትመንት ከተላለፈው 47ሺ 853 ሄክታር መሬት ውስጥ የለማው ከ28 ሺ ሄር በላይ እንደማይበልጥ የቤንች ሸኮ ዞን ንግድ እና ኢንበስትመንት መምሪያ አስታወቀ ።

Spread the love

የቤንች ሸኮ ዞን ዞናዊ የኢንቨስትመንት ፎረም መድረክ በሚዛን አማን ከተማ መካሄድ ጀምሯል።

“ኢንቨስትመንት ለሁለንተናዊ ብልጽግና “በሚል መሪ ቃል የቤንች ሸኮ ዞን ንግድና ኢንቨስትመንት መምሪያ በዞኑ ካሉ ባለሀብቶች ፣ አመራሮች እና አጋር አካላት ጋር የኢንቨስትመንት ፎረም መድረክ እያካሄደ ነው።

የዞኑ ዋና አስተዳደሪ አቶ ሀብታሙ ካፍትን በመድረኩ ባስተላለፉት መልዕክት በዞኑ ከጊዜ ወደ ጊዜ የኢንቨስትመንት ፍሰቱ እያደገ እንደሆነ ገልፀዋል

ዞኑ ካለው ለግብርና ልማት አመቺነት በዞኑ በሚገኙ ለም መሬት ለአለሚው ባለሀብት 47ሺ 853 ሄክታር መሬት በማስጠናት ማስተላለፍ ተችሏል።

በዚህም ለኢንድስትሪ እና በአገልግሎት ዘርፍ የተላለፈው መሬት ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ መልማቱን ጠቅሰዋል።

በግብርናው ዘርፍ ዞኑ ካለው አቅም አንፃርና ከተላለፈው መሬት አኳያ 28 ሺህ 467 ሄ/ር የለማ ሲሆን ቀሪው 19ሺህ 086 ሄ/ር እንዳለማ ገልፀዋል።

ያለንን ውስን የመሬት ሀብት በአግባቡ በመጠቀም ካልቻልን በመንግስተ፤ በህዝብና በራሳችን ላይ ከፍተኛ የሆነ ኪሳራን ማስከተላችን የማይቀር ነው ሲሉ ዋና አስተዳዳሪው ተናግረዋል።

ለኢንቨስትመንት አገልግሎት አሰጣጥ ባለድርሻ አካላት የዘመነ፣ ፈጣን፣ ግልፀኝነትና ተጠያቂነትን ያሰፈነ አሰራር በመከተል ዘርፉን ማነቃቃት ያስፈልጋል ያሉት ክብር አስተዳዳሪ

በፎረሙም አልሚ ባለሀብቶች የአካባቢን ፀጋ በመጠቀም የማህብረሰቡን ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ ባለፈ ለዘላቂ ሰላም ግንባታ ጉልህ ተሳትፎ በማድረግ የድርሻቸውን ለመወጣት የላቀ ሚና እንዳላቸውም ገልፀዋል።

ወደ ዞኑ ለሚመጡ ባለሀብቶች በግብርና በኢንድስትሪና በቱሪዝም የስራ ዘርፎች ለመሰማራት የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖሯቸውን ገልፀው ገብተው እንዲያለሙ ጥሪ አቅርበዋል።

በዞኑ ለሚኙ ከ37 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጐች ቋሚና ጊዜዊ የስራ እድል መፍጠር ችሏል ብለዋል፡፡

አክለውም የዞኑ አልሚ ባለሀብቶች ለሀገራዊ ልማቶች ገንዘብ በመስጠት እያደረጉ ያለው ተሳትፎና ድጋፍ ለሚጠየቁ ልማቶችና በዓላት ላደረጉት የተለያዩ ድጋፎች በዞኑ መንግስትና ህዝብ ስም የላቀ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

አቶ ኮጁ ባደከች የቤንች ሸኮ ዞን ንግድና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኃላፊ በመድረኩ እንደተና ገሩት ፎረሙ አልሚ ባለሃብቶችን ከዞኑ ከፍተኛ አስፈጻሚ አካላትና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ጋር በቀጥታ በማገናኘት በኢንቨስትመንት ዘርፉ በሚስተዋሉ ተግዳሮቶች ዙሪያ በጋራ በመምከር ለመፍታት ዕድል እንደሚፈጥር ተናግረዋል።

መምሪያው የንግድና ኢንቨስትመንት ስራዋችን በህግና በአሰራር የመምራት ተልዕኮ የተጣለበት እንደመሆኑ በዞኑ ውስጥ 312 የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች በግብርና በኢንድስትሪና በአገልግሎት ዘርፍ ተሠማርተው እየሰሩ እንደሆነ አቶ ኮጁ መግለጻቸውን የቤንች ሸኮ ዞን የመንግሰት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት መረጃ ያመለክታል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *