
የምክር ቤቱ አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ከነሷቸው ጥያቄዎች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል
. በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች ታጥቀው ከሚንቀሳቀሱ አካላት ጋር ልዩነቶችን በውይይት ለመፍታት ምን እየተሠራ ነው?
. የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት አፈጻጸም በምን ደረጃ ላይ ይገኛል? ፤ በትግራይ ዳግም ጦርነት እንዳይነሳስ ምን እየተሠራ ነው?
. የፍትሕ ተደራሽነት እና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ከመሰረቱ ለመፍታት መንግሥት በቀጣይ ምን ለመስራት አስቧል?
. በሰላም እጦት ሳቢያ በበርካታ የሀገሪቱ አካባቢዎች በሕዝብ ላይ የሚደርሰውን እንግልትን ከመሰረቱ ለመፍታት ምን እየተሠራ ነው?
. በአምራች ዘርፉ ያለውን የጥሬ ዕቃ እና የሌሎች የአቅርቦት ችግሮ ለመፍታት መንግሥት ምን እየሠራ ይገኛል?
. የ10 ዓመቱን ስትራቴጂክ ዕቅድ ማሳካት መቻላችን አመላካቾቹ ምን ምን ናቸው? ፤ ሴክተሮችስ ከዚህ ዕቅድ ጋር ተናብበው እየሠሩ ናቸው?
. መንግሥት በድጎማ የሚያቀርበው ነዳጅ በሕገወጥ መንገድ እንዳይሸጥ ለማድረግ ምን እየሠራ ይገኛል?
. በአሁኑ ሰዓት የመንግሥት ሠራተኛን ጨምሮ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ዜጎች በኑሮ ውድነት እየተቸገሩ ባሉበት ሁኔታ እንዴት የዋጋ ግሽበት ቀንሷል ይባላል?
. የቁጥጥር ተቋማት ነጻ ሆነው በትክክል ኃላፊታቸውን እንዲወጡ ለምን አይደረግም?
