




በዚሁ ዞናዊ የወጣቶች ክንፍ የውይይት መድረክ ከ400 በላይ ወጣቶች ተሣታፊ እንደሆኑ ለማወቅ ተችሏል።
በመድረኩ የካፋ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አጥናፉ ኃይሌን ጨምሮ የዞን እና የቦንጋ ከተማ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና የብልጽግና ወጣቶች ክንፍ ሥራ አስፈፃሚ አባላት እንድሁም ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት እየተሳተፉ ናቸው::
ተሣታፊ ወጣቶች ዜጎች በደም እጦት እንዳይሞቱ በሚል እሳቤ ፓርቲው ትኩረት ሰጥቶ ከሚተገብራቸው በጎ ሥራዎች አንዱ የሆነውን የደም ልገሣ ፕሮግራም ለማካሄድ ቅድመ ዝግጅት ተጠናቆ ለመለገስ በመጠባበቅ ላይ ናቸው::
በመድረኩ ሰነድ ቀርቦ መወያየትን ጨምሮ የተለያዩ መርሃ ግብሮች የሚከናወኑ ሲሆን የወጣቶች ክንፍ የውይይት መድረክ በተዋረድ እስከ ወረዳና ቀበሌ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ታውቋል ሲል የዘገበው የካፋ ዞን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው ።
