




በ2ኛ የብልጽግና ፓርቲ መደበኛ ጉባኤ አቅጣጫዎችና ውሳኔዎች ዙሪያ የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ የውይይት መድረክ በዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ ተካሄደ።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የብልጽግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽ/ቤት ፓለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ምክትል ኃላፊና የክልሉ ወጣቶች ክንፍ አስተባባሪ አቶ ዘርሁን ፍቅሬ ወጣቶች ገዥ ትርክትን በማፅናት ህብረ ብሔራዊ አንድነትን ለመገንባት ወጣቶች ያላቸው ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል።
አቶ ዘርሁን ከቃል እስከ ባህል በሚል መሪ ቃል ተግባራዊ በማድረግ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ ብልጽግና በማረጋገጥና በጠንካራ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሥራዎችን መሥራት አለብን ሲሉ አሳስበዋል።
የፓርቲያችን የመደመር ዕሳቤን መሠረት በማድረግ የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልጽግና እውን ለማድረግ በቀጣይ 3 ዓመታት ዘርፈብዙ መረሀ ግብሮች እንዳሉ በመጠቆም የወጣቱ ክንፍ ውይይት እስከ ታችኛው መዋቅር እየተከናወነ እንዳለ የወጣት ክንፍ አስተባባሪ አቶ ዘርሁን ፍቅሬ አስረድተዋል።
ዳውሮ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካና የህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ኢዮብ ቶማስ ወጣቶች የሀገር ባለበቶች ናቸው በማለት ወጣቱ በመቻቻልና በአርበኝነት መንፈስ 2ኛ የብልጽግና ፓርቲ መደበኛ ጉባኤ አቅጣጫዎችና ውሳኔዎች መሠረት የወጣቶችን ተጠቃሚነት ልያረጋግጡ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ ፓርቲው በትኩረት እንደሚሰራ አንስተዋል።
ወጣቶች በፖለቲካዊ፣በኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዘርፎች ላይ በማሳተፍ በመንግሥት የተጀመሩ የልማትና የመልካም አስተዳዳር ስራዎችን በመደገፍ የጋራ ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ ብልጽግናን እውን ማድረግ አለብን ሲሉ አቶ ኢዮብ ገልጸዋል።
አቶ ኢዮብ ወጣቶቱ ትኩስ ኃይል ከመሆኑ አንፃር ባላቸው እውቀት ሀገርን በሁሉም ዘርፍ ማገልገል እንደምገባ በመጠቆም ሚዲያን ለገዥ ትርክት በመጠቀም አፍራሽ አስተሳሰብን በአንድነት በመመከት የአከባቢውን ሠላም ማረጋገጥ አለብን ሲሉ አሳስበዋል።
ዳውሮ ዞን ወጣቶች ክንፍ ቅርጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ወጣት ዝናሽ ኃ/ማርያም በ2ኛ የብልጽግና ፓርቲ መደበኛ ጉባኤ አቅጣጫዎችና ውሳኔዎች ዙሪያ የወጣቶች ሚና የሚል የመወያያ ሰነድ ባቀረቡበት ወቅት ወጣቶች ገዥ ትርክትን በማፅናት ህብረ ብሔራዊ አንድነትን ለመገንባት የወጣቱ ሚና ከፍተኛ መሆኑን አንስተዋል።
በቀረበው ሰነድ መነሻ በመድረኩ የተሳተፉ ወጣቶች በበኩላቸው ሥራ አጥ ቁጡሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ የወጣቶች ስራ እድል ፈጠራ ላይ ትኩረት በማድረግ ወጣቱ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል።
ወጣቱ ከሚዲያ አጠቃቀም ዙሪያ ለልማትና ለበጎ አገልግሎት ለሰላም ግንባታ፣ ለልማት ስራዎች በመጠቀም የፓርቲውን ተልዕኮ በጋራ ለማሳካ የወጣቱ ክንፍ ትኩረት አድርጎ መስራት አለበት ሲሉ ተሳታፊዎች አንስተዋል።
በመድረኩ የዞን የታርጫ ከተማ አስተዳደር የታርጫ ዙሪያ ወረዳ የወጣት ክንፍ እና የዘርፉ አመራሩ ተሳታፊ ሆነዋል ሲል የዞኑ መንግስት ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።
