‘’የመጋቢታዊያን የለውጥ ፍሬዎችና የነገ ተስፋዎች!”በሚል መሪ ቃል በሸካ ዞን የዞን ማዕከል የብልፅግና ፓርቲ አባላት ኮንፈረንስ በቴፒ ከተማ ተካሄደ

Spread the love

ኮንፈረንሱን የመሩት በብልፅግና ፓርቲ ሸካ ዞን ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊና የዞኑ መንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አለማየሁ አለሙ እንደተናገሩት መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም በይፋ የለውጡ መንግስት በርካታና ውስብስብ ፈተናዎች እየተጋፈጠ አኩሪና እመርታዊ ለውጦችን እያስመዘገበ ወደፊት በመራመድ እነሆ ሰባተኛ ዓመቱን አስቆጥሯል ብለዋል።

ባለፉት 7 የለውጡ ዓመታት በርካታ ድሎች መመዝገባቸውን የገለፁት አቶ አለማየሁ ያጋጠሙትን ፈተናዎች ለመሻገር የተወሰደው መፍትሄም የሚደነቅ ነው ሲሉም ገልጸዋል።

በወርሃ መጋቢት 2010 ዓ.ም የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ቃለ መሃላ የፈጸሙበት ወር እና ሀገር መምራት የጀመሩበት መሆኑን ጠቁመዋል።

የመወያያ ሠነዱን ያቀረቡት በብልፅግና ፓርቲ ሸካ ዞን ቅ/ጽ/ቤት የፖለቲካና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊና ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ ዘርሁን አንደሞ በወቅቱ በሀገራችን የቆዩ ውስብስብ ችግሮችን ግምት ውስጥ ያስገባ፤ አሁን የምንገኝበትን ዓለም አቀፋዊና ሀገራዊ ሁኔታ የተገነዘበና የወደፊቱን መዳረሻ በውል ለይቶ ያስቀመጠ እንዲሁም ወደ መዳረሻችን የሚወስደንን መንገድ በመቀየስ ጉዞ የተጀመረ መሆኑን አንስተዋል።

ባለፉት 7 ዓመታት በግብርና፣ በኢንቨስትመንት፣ በገቢ፣ በከተማ ልማት፣በመንገድ ልማት እና በሌሎች ዘርፎች በርካታ አመርቂ ውጤቶች መመዝገባቸውን ጠቁመዋል አቶ ዘርሁን አንደሞ።

አቶ ዘርሁን አክለውም መጋቢት 24 በሀገራችን ታሪክ ሁለት ታላላቅ ሁነቶች የተስተናገዱበት ቀን ከመሆኑም አንጻር ይኸውም መላው የሀገራችን ህዝቦች ከዳር ዳር የደገፉትና የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልፅግና እውን ለማድረግ የሚያስችል ፖለቲካዊ ለውጥ የተደረገበት እና የለውጡ መሪ ክቡር ዶ/ር ዐብይ አሕመድ ሀገራችንን ለማስተዳደር በፓርላማው ፊት ቀርበው ቃለመሃላ የፈፀሙበት ቀን መሆኑ ገልፀዋል ሠነዱን ባቀረቡበት ወቅት።

የኮንፈረንሱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ባለፉት 7 የለውጡ ዓመታት በርካታ ድሎች መመዝገባቸውን ጠቁመው የአመራር ውጤታማነትና ስነ ምግባር በየወቅቱ እየተፈተሸ የሚመራ ከሆነ ከዚህም በላይ ውጤት ልኖር ይችላልም ብለዋል።

ከኑሮ ውድነትና ከህገወጥ ነዳጅ ግብይት አካባቢ ያለውን ጉዳይ አመራሩና የሚመለከታቸው ባለድርሻ ትኩረት ሰጥተው በመስራት ስርዓት ማስያዝ ቢችሉ የሚል አስተያየትም ሰጥተዋል ተሳታፊዎቹ።

በርካታ ጥያቄና አስተያየት ከተሳታፊዎች ተነስተው ከሚመለከታቸው አካላትና መድረክ መሪዎች ማብራሪያና ምላሽ ተሰጥቷል።

በኮንፈረንስ መድረኩ የሸካ ዞን ማዕከል ብልፅግና ፓርቲ አመራሮችና አባላት ተሳታፊ ሆነዋል ሲል የዞኑ መንግስት ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *