ለጠንካራ ፓርቲ ግንባታ መሰረት የሆነውን ጠንካራ ኢንስፔክሽን ለመፍጠር በትጋት መስራት እንደሚገባ ተገለጸ

Spread the love

‎የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የቦንጋ ማዕከል አስተዳደር ዘርፍ ህብረት ኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ኮሚሽን ኮሚቴ በህብረቱ ውስጥ ለሚገኙ የህብረትና ቤተሰብ አመራሮች በተሻሻለው በብልፅግና ፓርቲ መተዳደሪያ ደንብ፣ በኮሚሽኑ አሰራርና አደረጃጀት መመሪያ ዙሪያ የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጥተዋል ።

‎የህብረቱ ኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ኮሚሽን ሰብሳቢ ወ/ሮ ውቢት ደበበ ስልጠናውን አስመልክተው እንደገለጹት በብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ የተቀመጡ አቅጣጫዎችና ውሳኔዎችን ሳይቀራረፍ ውጤታማ ለማድረግ ትልቅ እገዛ እንደሚፈጥር ገልጸዋል።

‎ህብረቱ አመራሮች የተቀመጡ ዕቅዶችን ክለሳ በማድረግ በቀጣይ የተሻለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ በተናበበ መልኩ መስራት ይጠበቃል ብለዋል።

‎በተሻሻለው በብልፅግና ፓርቲ መተዳደሪያ ደንብና በሌሎች መመሪያዎችና አዳዲስ ድንጋጌዎች ላይ ስልጠና የሰጡት የኮሚሽኑ ህብረት ኮሚቴ አባል ወ/ሮ ውባለም በዛብህ እንደገለጹት የፓርቲው እሴቶች መርሆዎችን መሠረት አድርጎ በመስራት የብልጽግና ህብረት ኮሚሽን አመራሮች ግንባር ቀደም ሚናቸውን እንዲወጡም ገልጸዋል።

‎በየደረጃው የሚገኝ የፓርቲ ህብረትና የቤተሰብ አመራሮች የተግባርና አስተሳሰብ አንድነት በማጎልበት የውሰጠ ፓርቲ አንድነትን መፍጠር፣ በፓርቲው ውስጥ የፖለቲካ ጤንነት መጠበቁን መከታተልና ማረጋገጥ እንዲሁም

‎የኮሚሽኑን ተቋማዊ አቅም ሊያጠናክሩ የሚችሉ አሰራሮችና አደረጃጀቶችን ትኩረት ሰጥቶ መስራት አለብን ብለዋል።

‎የህብረቱ ኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ኮሚቴ ጸሃፊ የሆኑት አቶ አበበ ገ/ሚካኤል በተደጋጋሚ የሚጣሱ አሰራሮችን ሰነድ ላይ ባደረጉት ገለጻ በየደረጃው የሚገኙ የፓርቲና የኮሚሽኑ አደረጃጀቶችን የአሰራር ስርዓት በማክበርና በማስከበር ጠንካራ ፓርቲ ለመገንባት በሚደረገው እንቅስቃሴ ውስጥ ሚናችንን መወጣት እንደሚገባ ጠቅሰዋል።

‎የህብረቱ ኮሚሽን ሰብሳቢ አንድ ዕቅድ፣ አንድ ሪፖርት አንድ ሚዘና መርህን በመከተልና ለተግባራዊነቱ ሁሉም የህብረትና የቤተሰብ አመራሮች ሚናቸውን መወጣት እንዳለበቸው ገልጸዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *