




በምዕራብ ኦሞ ዞን በብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛው መደበኛ ጉባኤ ያሳለፋቸው ውሳኔዎች እና ያስቀመጣቸው አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረዉ የወጣቶች ክንፍ የዉይይት መድረክ በጀሙ ከተማ መካሄድ ጀምሯል።
በመድረኩ የክልሉ የኢንስፔክሽን እና ሥነምግባር ኮሚሽን ሃላፊ እና የወጣቶች ክንፍ አስተባባሪ አቶ ዳንኤል ያዙ እንደተናገሩት የወጣቶች ሁለተናዊ ተጠቃሚነት እና ገዢ ትርክት ግንባታ ላይ ሥራዎች እየተሰራ መሆኑ ተናግሯል።
ብልጽግና ፓርቲ በ2ተኛ መደበኛ ጉባኤ ያስቀመጣቸው አቅጣጫዎች ላይ በርካታ መድረኮች ሲካሄድ መቆየቱ አቶ ዳንኤል አዉስተው በውሳኔ እና አቅጣጫዎች ላይ የወጣቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑ አክሎበታል።
ወጣቶች ያላቸው ትኩስ ሃይል ለበጎ አላማ በመጠቀም ወንድማማችነት ህብረብሔራዊ አንድነት ላይ መሰረት ያደረገው ሥራዎች መስራት እንደሚገባ ተናግሯል።
ወጣቶች ልዩነቶች በመፀየፍ አንድነት እና አብሮነት በማጠናከር ለልማት ሥራዎች ግንባር ቀደም መሆኑ እንዳለባቸው ገልጸዋል።
የዞን የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ በድሉ መዓዛ በበኩላቸው ብልጽግና ፓርቲ ያስቀመጣቸው ግቦች እና ውሳኔዎች ወጣቶች የራሳቸውን ሚና በአግባቡ መወጣት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
የወጣቶች ዉይይት ከዞኑ ማዕከል ጀምሮ እስከ ቀበሌ ድረስ ከ31ሺህ በላይ ወጣቶች የሚሳተፉበት መድረኮች እየተደረገ መሆኑ ተናግሯል።
የዞኑ የወጣቶች ክንፍ ሃላፊ አቶ ፀጋለም ሳሙኤል የወጣቶች ተሳታፊነትና እና ተጠቃሚነት ላይ ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ ነው ብልዋል።
በዘላቂ ሠላም እና ልማት ላይ ወጣቶች የበኩላቸውን ሃላፊነት በአግባቡ መወጣት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
የተቀመጡ 10 ዋና ዋና ግቦች ላይ ዉይይት እንደሚደረግ የገለፁት አቶ ፀጋለም ወጣቱ በአግባቡ ተገንዝቦ በልማት እና በሠላም ሥራዎች ላይ ግንባር ቀደም ሚናቸውን መወጣት ይጠበቃል ብልዋል።
በጀሙ ከተማ ያለው መድረክ የዞን ማዕከል ወጣቶች የጀሙ ከተማ እና የመኤኒት ሻሻ ወረዳ ወጣቶች እየተገኙ ይገኛል።
