የትምህርት ስብራትን ለመጠገንና ቀጣይነት ያለውን ለውጥ ለማስመዝገብ የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ተሳትፎና ርብርብ ይጠይቃል፦አቶ አልማው ዘውዴ

Spread the love

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ከሸካ ዞን ትምህርት መምሪያ ጋር በመተባበር አጠቃላይ የትምህርት ስራዎች አፈፃፀምና የቀጣይ የሥራ አቅጣጫ ዙሪያ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር የውይይት መድረክ በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ እያካሄደ ይገኛል።

በምክክር መድረክ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አልማው ዘውዴ እንደገለፁት የትምህርት ስብራትን ለመጠገን፣ቀጣይነት ያለው ዕድገትን ለማረጋገጥ ብሎም ሀገር ተረካቢ ትውልድን ለማፍራት ውጤታማ ስራ መስራት ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ይጠበቃል ብለዋል።

ትውልድ ግንባታ ላይ መስራት ለሀገር ግንባታ ትልቅ መሠረት ነውና ለዘርፉ ስራ ስኬት የሁሉም ተሳትፎ ወሳኝ ነው ብለዋል አቶ አልማው።

የተማሪን ውጤት ለማሻሻል ትኩረት ሰጥቶ መስራት ይገባል ያሉት አቶ አልማው ዘውዴ በዘላቂነት የትምህርት ጥራትን ማረጋገጥ የምንችለው ከቅድመ 1ኛ ደረጃ ጀምሮ መስራት ስንችል በመሆኑ ልዩ ትኩረትን ይሻል ሲሉ ገልፀዋል።

በክልሉ እየተተገበሩ ያሉ የትምህርት ዘርፍ ስራ ውጤት እያስመዘገበ መሆኑን የጠቆሙት አቶ አልማው ዘውዴ የተጀመረው ጥረት የተፈለገውን ውጤት እንዲያመጣ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም በአፅንኦት ጠይቀዋል።

በክልሉ የትምህርት ስብራትን ለመጠገን በርካታ ስራዎች እየተተገበሩ መሆኑን ተናግረው የትምህርት ጥራት እንዲረጋገጥና የተጀመረው ስራ የተጠናከረ እንዲሆን በየደረጃው ያሉ የትምህርት ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ድርሻ ሊወጡ ይገባልም ብለዋል።

በመድረኩ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ ማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አልማው ዘውዴ፣የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዶክተር ደስታ ገነሜን ጨምሮ የዞን፣የወረዳ/ከተማ ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች፣ሱፐርቫይዘሮች፣ርዕሰ መምህራንና የትምህርት ዘርፍ አመራሮች እየተሳተፉ ይገኛል ሲል የዞኑ መንግስት ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *