በምዕራብ ኦሞ ዞን በወርሃ መጋቢት ትሩፋቶች ዙሪያ የአስተዳደር ዘርፍ የብልጽግና ፓርቲ ህብረት የዉይይት መድረክ ተካሄደ

Spread the love

በመድረኩ የዞኑ የፐብሊክ ሰርቪስ እና ሰው ሃብት ልማት መምሪያ ሃላፊ አቶ አሸናፊ እንደተናገሩት በወረ መጋቢት ላይ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ቃለ መሃላ የፈጸሙት ወር እና ሀገር መምራት የጀመረበት መሆኑ አውስተዋል።

መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም በይፋ የለውጡ መንግስት በርካታና ውስብስብ ፈተናዎች እየተጋፈጠ አኩሪና ዕምርታዊ ድሎች እያስመዘገበ ወደፊት በመራመድ እነሆ ሰባተኛ ዓመቱን የተቆጠረበት መሆኑ ተገልጿል።

በሀገራችን የቆዩ ውስብስብ ችግሮችን ግምት ውስጥ ያስገባ፤ አሁን የምንገኝበትን ዓለም አቀፋዊና ሀገራዊ ሁኔታ የተገነዘበና የወደፊቱን መዳረሻ በውል ለይቶ ያስቀመጠ እንዲሁም ወደ መዳረሻችን የሚወስደንን መንገድና አቅጣጫ በመቀየስ መንገዱን መጀመሩን ተጠቅሷል።

የዞኑ የአስተዳደር ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ኑሩ ኢብራሂም በበኩላቸው መንግስት በባለፈው አመታት በግብርና በኢንቨስትመንት በማዕድን በገቢ እና በሌሎች ዘርፎች በርካታ ሥራዎች ሰርቷል አሁንም እየሰራ ይገኛል ብልዋል።

መጋቢት 24 በሀገራችን ታሪክ ሁለት ታላላቅ ሁነቶች የተስተናገዱበት ቀን ነው ከመሆኑም አንጻር ይኸውም መላው የሀገራችን ህዝቦች ከዳር ዳር የደገፉትና የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልፅግና ዕውን ለማድረግ የሚያስችል ፖለቲካዊ ለውጥ የተደረገበት እና የለውጡ መሪ ክቡር ዶ/ር ዐብይ አሕመድ ሀገራችንን ለማስተዳደር በፓርላማው ፊት ቀርበው ቃለ-መሃላ የፈፀሙበት ቀን መሆኑ ተገልጿል።

ብሔራዊ ጥቅማችንን ለማስጠበቅ የተደረገውን ተጋድሎ፤ በምግብ እራስን ለመቻል ያደረግነውን እንቅስቃሴና የተገኘውን ውጤት፤አበረታች መሆኑ ተገልጿል።

ገቢያችንን በማሳደግ ኢኮኖሚያችንን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ያደረግነውን ጥረት፤ በኢነርጂ ዘርፍ ያደረግነውን እምርታ በአምራችነት ሉዓላዊነትን ስለማስከበር የምንዘክርበት እና ከዚህ በመነሳት ለአዲሱ ዕምርታዊ ጉዞ የምንዘጋጅበት ቀን አድርገን ልንወስደው ይገባል ነው ያሉት።

የነገው ቀን ብሩህና መጭው የመደመር ትውልድ የተሻለች ኢትዮጵያን ለመፍጠር የሚኖራቸውን ኃላፊነቶች አባላቶች በአግባቡ መወጣት እንዳለባቸው ተገልጿል።

በመድረኩ የአስተዳደር ዘርፍ የብልጽግና ፓርቲ ህብረት አመራሮች እና አባላቶች ተገኝተው ሰነድ ቀርቦ ዉይይት ተደርጎበታል ሲል የዞኑ መንግስት ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *