ብልፅግና ፓርቲ ዘላቂ የልማት እና የመልካም አስተዳደር ተግባራትን አቅዶ ከመፈፀም ባሻገር አዳዲስ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ በማነቃቃት የለውጥ ጉዞን አጠናክሮ እያስቀጠለ ያለ ፓርቲ መሆኑ ተገለፀ

Spread the love

የካፋ ዞን ማዕከል የብልፅግና ፓርቲ የመንግስት ሰራተኞች የሁሉም ህብረት አባላት መጋቢት 24 ቀንን አስመልክቶ “የመጋቢታዊያን የለውጥ ፍሬዎችና የነገ ተስፋዎች” በሚል መሪ ሀሳብ በቦንጋ ከተማ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።

የአስተዳደር ዘርፍ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚ ዘርፍ የብልጽግና ፓርቲ የዞን ማዕከል የመንግስት ሰራተኞች ህብረት አባላት በየህብረታቸው የመጋቢታዊያን የለውጥ ፍሬዎችና የነገ ተስፋዎች በሚል ሀገራዊ አጀንዳ ላይ ሰነድ እየቀረበ ሲሆን በሰነዶች ላይ ውይይት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል::

የአስተዳደር ዘርፍ ብልጽግና ህብረት መድረክ ላይ ሰነድ የያቀረቡት አቶ ዘመዴ አንዳርጌ እንዳሉት መጋቢት ወር በሀገራችን በሁሉም ዘርፍ የለውጥ አሻራ የተቀመጠበት ታሪካዊ ወር ከመሆኑም በላይ ብልፅግና ፓርቲ ዘላቂ የልማት ተግባራትን አቅዶ በመፈፀም አዳዲስ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ በማነቃቃት የለውጥ ጉዞን አጠናክሮ እንድያስቀጥል መነሻ የሆነች ወር ነች በሏል::

በወርሃ መጋቢት የተጀመረው የለውጥ ጉዞው በርካታ ተግዳሮቶችን አና ፈተናዎችን እየተጋፈጠ ያንኑ በመቋቋም ዘርፈ ብዙ ውጤት ማስመዝገብ የቻለ ብልጽግና ፓርቲ የተወለደበትም ወር መሆኑ በሁሉምብልጽግና ህብረት መድረኮች በአጽንኦት እየተነሳ ይገኛል።

የፓርቲውን የለውጥ ጉዞ የተመለከተ ሰነድ በሁሉም መድረኮች በዞኑ በተለያዩ የስራ ኃላፊዎች እየቀረበ የሚገኝ ሲሆን ይህንኑ ተክትሎ ውይይት የሚደረግ ይሆናል ሲል የዞኑ መንግስት ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *