በቤንች ሸኮ ዞን በሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ድጋፍ እያደረገ የሚገኘዉ የክልሉ የሱፐርቪዥን ቡድን በሚዛን አማን ከተማ ከተለያዩ ማህበራዊ መሰረቶች ከተወጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ተወያዩ

Spread the love

በክልሉ ማዕድንና ኢነርጂ ልማት ቢሮ ሃላፊ ኢ/ር በየነ በላቸው የተመራ የክልሉ አመራር ቡድን በቤንች ሸኮ ዞን በሚዛን አማን ከተማ በመንግስትና በፓርቲ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን አስመልክቶ ከነዋሪዎች ጋር ውይይት አካሂዷል።

የመድረኩ አላማ በሁሉም አካባቢዎች እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ወደ ታች በመውረድ በአካል ከመመልከት በተጨማሪ የተጠቃሚዉንና የተገልጋዩን ማህብረሰብ ቀጥተኛ አስተያየት በማዳመጥ የልማትና መልካም አስተዳደር ችግሮችን በየደረጃው መፍታት በማስፈለጉ መድረኩ መመቻቸቱ ተገልጿል።

በሚዛን አማን ከተማ የልማት፣የመልካም አስተዳደርና የህብረተሰብ ተሳትፎ ማረጋገጥን በተመለከተ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ለማጠናከርና ለማፋጠን ወደ ኃላ ያልተሰሩና በእቅድ የተካተቱትን በቀጣይ በትኩረት ለመስራት ነዋሪዉን በማወያየትና ከውይይቱ የተገኙ ግብአቶችን በማከል አቅዶ መስራት አስፈላገመ መሆኑም ተጠቅሷል።

በውይይት መድረኩ ከእሁድ ገበያ ጋር በተያያዘ የሚቀርቡ የግብርናና የፋብሪካ ምርቶች ብዛትና አይነት ውስን መሆኑ ሸማቹ የሚፈልገውን በተመጣጣይ ዋጋ ሸምቶ ለመጠቀም በሚያስችል መልኩ ልዩ ልዩ ምርቶችን ያካተተ ሊሆን ይገባል ተብሏል።

ከኮሪደር ልማት ጋር በተያያዘ የሚሰሩ ስራዎች ለቀጣይ ትውልድ የሚተርፉ ቢሆንም ወጥነት ባለው መልኩ ከልየታ ጀምሮ በትኩረት ሊሰራና ከባለይዞታዎች ጋርም የውይይት መድረኮችን ማጠናከር አስፈላጊ መሆኑ ተመላክቷል።

በመድረኩ የተሳተፉት የከተማዉ ነዋሪዎች ዞናዊና ከተማን የተመለከቱ የመሰረተ ልማት፣የአገልግሎት አሰጣጥ፣የኮሪደር ልማት፣ የኑሮ ዉድነትን፣ የውሃ ተደራሽነት፣ የመድሃኒት አቅርቦትና የጤና ተቋማት የአገልግሎት አሰጣጥ፣ የወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ የኢንቨስትመንት ዉጤታማነትን የተመለከቱ ጉዳዮች ላይ አስተያየትና ጥያቄ አንስተዉ ዉይይት መደረጉን የከተማ አስተዳደሩ ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *