የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ እና ኢንዱስትሪና ኢኖቬሽን ቢሮ የትራንስፖርት አገልግሎትን ዲጂታል ለማድረግ በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ

Spread the love

የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ከክልሉ ኢንዱስትሪና ኢኖቬሽን ቢሮ ጋር በመተባበር የትራንስፖርት ዘርፉን የአገልግሎት አሰጣጥ ለማሳደግ ቴክኖሎጂን መጠቀም ዙሪራ ውይይት አደርገዋል።

በፊርማ ስነስርዓቱ ላይ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ መሠረተልማት ክላስተር አስተባባሪና የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ፋጂዎ ሳፒ በህዝብ ትራንስፖርት ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት ዲጂታል መፍትሄዎችን መቀበል ወሳኝ መሆኑን ገልፀዋል።

የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አሸብር ኢካሎ በበኩላቸው በክልሉ በየዓመቱ 13 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች በሕዝብ መጓጓዣ ላይ ጥገኛ ናቸው ብለው እያደገ የመጣውን ፍላጎት ለማስተናገድ የአገልግሎት ጥራትን ለማሻሻል ቴክኖሎጂን መጠቀም አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።

የክልሉ ኢንዱስትሪና ኢኖቬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ግዛው ጋግያብ በትራንስፖርት ዘርፍ የህብረተሰቡን እርካታ ማሳደግ ከዘመናዊ ቴክኖሎጂ ውጭ መሆን እንደማይቻል ገልጸው በቀጣይም ቢሮአቸው ከፌዴራል መንግስትና ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመተባበር ውጤታማ እና ቀልጣፋ የቴክኖሎጂ መፍትሄዎችን ለማቅረብ እየሠራ መሆኑን ተናግረዋል።

የክልሉ ኢንዱስትሪና ኢኖቬሽን ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ምትኩ አስፋው በበኩላቸው የትራንስፖርት ዘርፉ ለዲጂታል ውህደት ወሳኝ ከሆኑ መስኮች አንዱ መሆኑን መናገራቸውን ከኢንዱስትሪና ኢኖቬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *