#ሪፖርታዥ

Spread the love

በ 252 ቀበሌዎች ላይ ባህላዊ የዳኝነት አደረጃጀት ተፈጥሯል:-የክልሉ ፍትህ ቢሮ

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ባለድርሻ አካላት ያሳተፈ የግንዛቤ ሥራ በመሰራቱ በክልሉ 252 ቀበሌዎች ላይ የባህላዊ ዳኝነት አደረጃጀት ተፈጥሮ ወደ ተግባር እየገቡ እንደሚገኙ የክልሉ ፍትህ ቢሮ አስታውቋል፡፡
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ እሸቱ ጎዴቶ ሀገሪቱ በአለም አቀፍ የሰብኣዊ መብት ስምምነቶች ከገባችባቸው ግዴታዎች ጋር የተጣጣሙ ሕጎች እንድኖራት እና የዜጎች የዕለት ተዕለት ኑሮ እና የሰብዓዊ መብት ላይ ተጽዕኖ ያላቸው ሕጎች በማሻሻል ረገድ ትልቅ ስራ መሰራቱን አብራርተዋል ፡፡
ድህረ-2010 የተደረጉት የሕግ ማሻሻያ ጥረቶች ሁሉ በሀገሪቱ በተፈጠረ የፖለቲካ ምህዳር ለውጥ አማካኝነት የመጡ ናቸው።የለውጥ መንግስት በቅድሚያ ለህዝቡ ከገባቸው ቃሎች መካከል በዴሞክራሲ ግንባታ ረገድ ሰፊ ማሻሻያዎችን የሚያደርግ መሆኑ ዋነኛው ስለመሆኑም አቶ እሸቱ ጎዴቶ አብራርተዋል ።
እነኚህ የሕግ ማሻሻያ ስራዎች ሀገሪቱ በአለም አቀፍ የሰብኣዊ መብት ስምምነቶች ከገባችባቸው ግዴታዎች ጋር የተጣጣሙ ሕጎች እንድኖራት እና የዜጎች የዕለት ተዕለት ኑሮ እና የሰብዓዊ መብት ላይ ተጽዕኖ ያላቸው ሕጎች በማሻሻል ረገድ ትልቅ ስራ ስለመሰራቱም አብራርተዋል ፡፡
የሕግ ማውጣት ሂደቱ የዜጎችን ተሳትፎ እንዲያረጋግጥ ጥረት መደረጉ ለአብነት የሚጠቀስ ነዉ ሲሉም ገልጸዋል፡፡ በዚሁ መሠረት የሕግ ማሻሻያ ስራዎችን በመለየት በተለይ አፋኝ እና ገዳቢ የነበሩ እና ለአገዛዝ አላማ ታስበው የወጡ ሕጎችን በመለየት የማሻሻያ ስራዎች ተሰርቷል ብለዋል፡፡
የተደረጉት የሕግ ማሻሻያዎችም የሲቨክ ማህበራት ሕግ መሻሻሉ፣ የወንጀል ፖሊሲ መውጣቱ፣ የጥብቅና አገልግልት ሕግ መሻሻሉ፣ የኢትዮጵያ አገራዊ ሰብአዊ መብቶች የ5 ዓመት ዕቅድ መዘጋጀቱ፣የምርጫ ህግ መሻሻሉ እና የጸረ- ሽብር ህግ መሻሻሉ ለአብነት የሚጠቀሱ ናቸዉ ማሻሻዮች ስለመሆናቸውም አቶ እሸቱ አብራርተዋል ፡፡
የህዝባችንን የፍትህ ጥማት የሚያረካ ዜጎች የሚተማመኑበት የፍትሕ ሥርዓት መፍጠር ላይ መንግስት ከፍተኛ ርብርብ እያደረገ ይገኛል ያሉት አቶ እሸቱ የፍትሕ ሥርዓቱን የማዘመን፣ ብቁ ባለሙያዎችን የመመደብ፣ ፈጣንና አስተማማኝ አገልግሎት እንዲሰጥ የማስቻል፣ የፍትህ አካላት ነጻነትንና ተጠያቂነትን በሚዛን የማረጋገጥ ተግባራት በትኩረት እየተሰሩ ናቸዉ ሲሉም ገልጸዋል ።
ለዚህም የፍትሕ ትራንስፎርሜሽን እቅድ ትግበራን የማጠናከር እንደ ዋና መሳሪያ በመጠቀም እንደ ሀገር በጥናት ላይ ተመስርቶ በተዘጋጀዉ የሶስት ዓመት የፍትህ ሥርዓት ማሻሻያ ፍኖተ ካርታ መነሻ የክልሉን ነባራዊ ሁኔታ መነሻ ያደረገ የሦስት ዓመት ክልላዊ የፍትህ ዘርፍ ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ/ፍኖተ ካርታ/ ተዘጋጅቶ ወደ ተግባር መገባቱንም ተናግረዋል፡፡
የፍኖተ ካርታዉ ዋና ዓላማ በክልሉ ፍትህ ዘርፍ ተቋማት የሚካሄዱ ማሻሻያ/ሪፎርም በተቋማቱ እስካሁን የተሠሩ ጠንካራ ጎኖችን የበለጠ በማጠናከር በድክመቶች ላይ ተገቢውን እርምጃ በመውሰድና በማረም በሕዝቡ ዘንድ ተቀባይነትና ተኣማኒነት ያለው ጠንካራ ተቋም በመፍጠር የተገልጋዩን እርካታ ማሳደግ ነዉ፡፡
በዚሁ ዓላማ የታቀደዉ ፍኖተ ካርታዉ 10 ዋና ዋና አምዶች የያዘ ሆኖ ከዕቅድ ዝግጅት ከግንዛቤ መፍጠር እና ሌሎችም ሰፊ የቅድመ ዝግጅት ምዕራፎችን በማለፍ ከአምዶቹ ለምሳሌ በመሠረተ ማህበረሰብ የፍትህ አገልግሎት አምድ የባህላዊ ፍርድ ቤቶችን ለማቋቋም እና እዉቅና ለመስጠት የሚያችል አዋጅ ለክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት ቀርቦ ዉይይት ተደርጐ ለክልሉ ምክር ቤት ቀርቦ በአዋጅ ቁጥር 35/2016 በመሆን ፀድቋል በማለትም አብራርተዋል፡፡
አዋጁን ወደ ተግባር ለማስገባት የሥራዉ ባለቤት የሆኑት ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና የክልል ምክር ቤት አንድሁም ሌሎችም የክልል ባለድርሻ አካላት ባሉበት ዞን ባለድርሻ አካላትና ባለቤቶችን በመጥራት የግንዛቤ ሥራ በመሰራቱ በክልላችን 252 ቀበሌዎች ላይ የባህላዊ ዳኝነት አደረጃጀት ተፈጥሮ ወደ ተግባር እየገቡ እንደሚገኙም አቶ እሸቱ ገልጸዋል ፡፡
የማህበራዊ ፍርድ ቤት አዋጅም የዚሁ የትራንስፎርሜሽን አካል የሆነዉ የስራ ነገር ሥልጣን ተሸሽሎ ፀድቆ ተግባራዊ ሆኗል፡፡ በክልሉ ዜጎች ከአሰተዳደራዊ ጉዳይ የሚመነጩ ቅሬታዎቻቸውና አቤቱታዎች ላይ የመንግስት አሰራር በግልጽነትና ተጠያቂነት ባለው መልኩ እንዲፈታና እነዚህ ማዕቀፎች መፍትሔ መስጠት በማይችሉበት ጊዜ በማናቸውም አስተዳደራዊ ውሳኔዎች ላይ የፍ/ቤት ክለሣን ያስተዋወቀ አስተዳደር ሥነ-ሥርዓት አዋጅም ፀድቆ በአዋጁ መሠረት 26 መመሪያዎች ለፍትህ ቢሮ ቀርበዉ እንዲመዘገቡ ተደርጓል፡፡
ቀጣይ ባልተሰሩ አምዶች በተለይም የፍትህ ዘርፍ አመራሮችና ባለሙያዎችን ማጥራት አምድ ላይና በሌሎችም በትኩረት የሚሰራ ይሆናል ሲሉም አቶ እሸጹ ጎዴቶ አብራርተዋል ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *