የ2017 በጀት ዓመት የበልግ ልማት የዘር ሳምንት ማስጀመሪያ መረሃ ግብር ተካሄደ

Spread the love

የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በካፋ ዞን ጊምቦ ወረዳ የበልግ ልማት ወረዳዊ የቦቆሎ ክላስተር የዘር ማስጀመሪያ መረሐግብር አከናውኗል።

የክልሉ ዋና የመንግሥት ተጠሪ አቶ ፍቅሬ አማን፣ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸዉን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች የ2017 ዓ.ም ክልላዊ የበልግ ልማት የበቆሎ ክላስተር ዘር አስጀምረዋል።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በ2017 ዓ.ም በልግ ምርት ዘመን 359 ሺህ ሄክታር ማሳ በተለያዩ ሰብሎች እንደሚለማ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸዉ ገለጹ።

በዚሁ ወቅት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸዉ ክልሉ የበልግ አዝመራ በስፊዉ የሚከናወንበት አካባቢ ነዉ ብለዋል።

በዘንድሮ በ2017 በልግ ምርት ዘመን 359 ሺህ ሄክታር ማሳ በተለያዩ ሰብሎች ከሚሸነፈው ውስጥ 245 ሺህ ሄክታር ቦቆሎ እንደሚለማና ከዚህም ውስጥ 95 ሺህ ሄክታር ማሳ በካፋ ዞን እንደሚለማ አቶ ማስረሻ በላቸዉ ተናግረዋል።

በካፋ ዞን ጊምቦ ወረዳ ሾምባ ሼካ ቀበሌ ከዚህ በፊት የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ተግዳሮት እንደነበረና አሁን ላይ መሻሻሎች መኖሩን አንስተዉ የአካባቢው አርሶ አደሮች የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ባህላቸዉን በማሻሻል የግብር ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ ትኩረት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።

የክልሉ መንግሥት ክልሉ ከተመሠረተ ጊዜ አንስቶ አርሶአደሮችን በመደገፍ ፣ለእርሻ ሥራዎች ግብዓት የሚሆኑ ምርጥ ዘሮችና ማዳበሪያዎችን በወቅቱ በማቅረብ እንዲሁም የመስኖ አውታሮችን በመዘርጋት የግብርና ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እያደረገ ባለዉ ስራ ውጤቶች እየተመዘገቡ መሆናቸዉን የክልሉ መንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ፍቅሬ አማን ገልጸዋል።

በክልሉ ጊምቦ ወረዳ ሾምባ ሼካሸ ቀበሌ 600 ሄክታር የሚለማ ሲሆን ከዚህ ዉስጥ ደግሞ 122 ሄክታር የሚደርስ በኩታገጠም የሚለማው የበቆሎ አዝመራ ቀጣይ ትልቅ ውጤት የሚጠበቅ ነዉ ያሉት አቶ ፍቅሬ አማን ተግባሩ በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች በስፋት የሚተገበር ይሆናልም ብለዋል።

ምርትና ምርታማነት ሊያሳድግ የሚችሉ በኩታ ገጠም ከማረስ ቀጥሎ መካናይዘሽን በመጠቀም የተለያዩ ግብዓቶችን በመጠቀም አዝመራውን በተገቢው በመንከባከብ ምርቱ ሲደርስ በወቅቱ ሊሰበሰብ እንደሚገባ አሳስበዋል አቶ ፍቅሬ አማን።

የካፋ ዞን ዋና አስተዳደሪ አቶ እንዳሻዉ ከበደ በካፋ ዞን በ2017 በልግ ምርት ዘመን በኩታገጠም እና በሜካናይዝድ እርሻ የተለያዩ ምርትና ምርታማነት ሊያሳድጉ የሚችሉ የግብርና ቴክኖሎጂ በመጠቀም ምርታማነትን ለማሳደግ ይሰራልም ብለዋል።

በፍቅር ከበደ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *