ክልላዊ ነበራዊ ሁኔታን መሠረት ያደረገ የአጠቃላይ አመራር ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል፥ የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የክልሉን ነባራዊ ሁኔታ መሠረት ያደረገ የአጠቃላይ አመራር የአቅም ግንባታ ውይይት በቦንጋ ከተማ እያካሄደ ይገኛል።

በውይይቱ መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የክልሉ የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ፍቅሬ አማን፥ የአቅም ግንቦት መድረኩ ያስፈለገው ባለፋት ጊዜያት በተሰጡ ስልጠናዎች፣ በተፈጠሩ ህዝባዊና የአመራር መድረኮች የተገኙ ልምዶች በማቀናጀት የክልሉ እምቅ ፀጋ በተሟላ መልኩ ወደ ሚጨበጥ ሀብት ለመቀየር ያለመ መሆኑን አመላክተዋል።

“የአስተሳሰብ ልዕልና፣ ለሁለንተናዊ ብልጽግና” በሚል መርህ ቃል የተዘጋጀው የአቅም ግንባታ ውይይት መድረክ በአመራር መካከል የአስተሳሰብና የተግባር አንድነትን በማጠናከር የህዝብ የልማት አቅሞችን አቀናጅተው ወደ ተግባር እንዲገባ የሚያስችል እንደሆነም ነው አቶ ፍቅሬ የገለጹት።

መድረኩ የክልሉን አጠቃላይ ነባራዊ ሁኔታ በዝርዝር በመተንተን እና በየደረጃው ያለውን አመራር የመፈጸምና የማስፈጸም አቅም በማጠናከር ውጤታማ እንዲሆን ለማድረግ ያለም እንደሆነ ያብራሩት አቶ ፍቅሬ መሰል የፖለቲካ አዝማሚያን በጥልቀት በመገምገም የተግባቦት አቅጣጫ የሚያስቀምጡ መድረኮች በየደረጃው ባለው መዋቅር መካሄድ እንደሚገባቸዉ አንስተዋል።

የአመራር የአስተሳሰብ ጥራት በማሻሻል የተግባር ውጤታማነት ማሳደግ እንደሚገባ የገለጹት አቶ ፍቅሬ ከመድረኩ ክልላዊ አንድነት በማጠናከር የተግባር አፈጻጸም ለማሳደግ የሚረዳ ትምህርት የሚወሰድበት እንደሆነ ጨምረው ገልጸዋል።

በዕድገቱ በዛብህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *