የክልሉ መንግሥት ለ1 ሺህ 216 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት የመጪውን ፋሲካ በዓል ምክንያት በማድረግ ለ1216 ታራሚዎች ይቅርታ አድርጓል።

በክልሉ ባሉ ማረሚያ ቤቶች በህግ ፍርድ አግኝተዉ ሲታረሙና ሲታነጹ ከቆዩ ታራሚዎች መካከል የይቅርታ ጥያቄ ካቀረቡት ወስጥ የይቅርታ አዋጅ፤ደንብና መመሪያ መሰረት መስፈርቱን ያሟሉ ታራሚዎችን ማመልከቻ የይቅርታ ቦርዱ ከመንግስት ፤ከህዝብ ና ከታራሚ ጥቅም አንፃር በማገንዘብ በጥልቀት መርምሮ ወንድ 1183 ሴት 33 ድምር 1216 ታራሚዎች የይቅርታ ተጠቃሚ መሆናቸው ነው የተገለጸው።

የይቅርታ ተጠቃሚዎች በማረሚያ ተቋሙ በነበራቸዉ ቆይታ ስለመታረማቸዉ ፤ስለመታነጻቸዉና ስለመልካም ባህሪያቸዉ በየደረጃዉ ከሚገኙ የፀጥታ ተቋማት በቂ ማረጋገጫ የተሰጣቸዉ እንደሆነም ተመላክቷል።

ይቅርታ ጥያቄያቸዉ ተቀባይነት አግኝቶ ከእስር የሚለቀቁ ታራሚዎች ለወደፊቱ ለህብረተሰቡ የወንጀል ስጋት ሳይሆኑ የሠላም ሰባኪ፤ አምራችና ህግ አክባሪ ዜጋ ሆነዉ ህብረተሰቡን እንዲቀላቀሉና ህብረተሰቡም ስለመታረምና መታነፃቸዉ አዉቀዉ እንዲቀበላቸዉ እና ከወጡ በኃላ የይቅርታ ዓላማ የማያሳኩ ተጠቃሚዎች ካጋጠሙም ህብረተሰቡ በተለመደዉ ጨዋ አካሄድ ተገቢዉን መረጃ በየደረጃዉ ላሉ ፍትህ አካላት እንዲሰጥ ተጠይቋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *