የፓርቲው ተቋማዊ አቅምን ለማጠናከር የብልጽግና ቤተሰብና ህብረት ለፓርቲ ተቋም ግንባታ መሠረት የሚጥል ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል።

Spread the love

‎የፓርቲው ተቋማዊ አቅምን ለማጠናከር የብልጽግና ቤተሰብና ህብረት ውጤታማና መሠረት የሚጥል ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ የቦንጋ ማዕከል የአስተዳድር ዘርፍ የብልጽግና ህብረት ሰብሳቢ አቶ ሳምሶን መለሰ ገለጹ።

‎በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የቦንጋ ማዕከል የአስተዳደር ዘርፍ የብልፅግና ህብረት የሱፐርቪዥንና ድጋፋዊ ክትትል ምልከታ ያካሄደውን ግብረ-መልስ ሪፖርት ግምገማ እያካሄደ ነው።

‎የቤተሰብ አደረጃጀትና አሰራር፣ አዳዲስ አባላት ምልመላ፣ የአባላት ቅሬታዎችና አቤቱታዎች ስለመፈታታቸው፣ ገቢ አሰባሰብ፤የፓርቲና የመንግስት ሥራዎችን በግንባር ቀደምትነት ከመፈጸም አንጻር የነበረው ሁኔታ ምልከታ አካሂዷል።

‎የህብረቱ ሰብሳቢ አቶ ሳምሶን መለሰ የህብረቱ አመራሮች የብልጽግና ቤተሰብ እያከናወነ ያለውን እንቅስቃሴ በአካል ተገኝቶ ከመረዳት ባሻገር የታዩ ጥንካሬዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል እና ክፍተቶችን ፈጥኖ ለማረም እንዲሁም በቀጣይ ተነሳሽነትን በመፍጠር የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ ዓላማ ያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

‎የብልጽግና ቤተሰብ የውሰጠ ፓርቲ አንድነትን በማጎልበት ጠንካራ ፓርቲ ለመገንባት የተጀመሩ ተግባራትን አርአያ በመሆን በላቀ ቁርጠኝነት መተግበር ያስፈልጋል ብለዋል።

‎የአስተሳሰብና የተግባር አንድነትን በማጠናከር በተሰማሩበት የስራ መስክ የብልጽግና ራዕይ፣ ዓላማ ፣ እሴት፣ አሻጋራ ሀሳቦችን የዕለት ተዕለት ተግባር በማድረግ ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ ብርቱ ትግል ማድረግ እንደሚገባ ጠቅሰዋል።

‎የብልጽግና ቤተሰቦች በአደረጃጀቶች አሰራር ስርዓት መሠረት ውይይቶች በጥራትና በብቃት በማካሄድ ይገባል ብለዋል።

‎በመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚታዩ ብልሹ አሰራርና የአገልግሎት ችግሮችን ለማስተካከልና ለማሻሻል የብልጽግና ቤተሰቡ ሚናውን መወጣት እንዳለበት ገልጸዋል።

‎በድጋፋዊ የሱፐርቪዥን ቡድን በተደረገው ምልከታ የተገኙ ግኝቶችንና ምክረ ሀሳቦችን መሰረት በማድረግ ስኬቶችን ለመቀመር፣ጉድለቶችን በማረም ለቀጣይ ስራ ተነሳሽነት የሚፈጥር እንደሆነ በማስገንዘብ የውይይት መድረክ ተጠቃሏል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *