




የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የኢኮኖሚ ክላስተር የ2017 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው በተገኙበት እየተገመገመ ይገኛል።
በዚህም የኢኮኖሚ ክላስተር ስር የሚገኙ ተቋማት የገቢዎች ቢሮ፣የፕላንና ልማት ቢሮ፣ የኢንዱስትሪና ኢኖቬሽን ቢሮ ፣የንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ ፣የደን፣አካባቢ ጥበቃና የአየር ንብረት ለውጥ ቢሮ፣የግብርና ቢሮ፣የፋይናንስ ቢሮ፣ እንዲሁም የስራና ክህሎት ቢሮ የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈፃፀማቸውን እያቀረቡ ነው።
በቀጣይ፣ሪፖርቱ ላይ ውይይት በማድረግ የቀጣይ አቅጣጫ እንደሚቀመጥም ተጠቁሟል።
በካሳሁን አሰፋ
