የክልሉ ኦዲት አስመላሽ ግብረሃይል በየጊዜው በሚያካሂዳቸው ግምገማዎች እና በሚያስቀምጣቸው አቅጣጫዎች በኦዲት ግኝት ላይ ውጤቶች እየተመዘገቡ ነዉ ፦ የተከበሩ ዋና -አፈጉባኤ አቶ ወንድሙ ኩርታ

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፋይናንስ ቢሮ እና የክልሉ ምክር ቤት በጋራ አዘጋጅነት የኦዲት አስመላሽ ግብረሃይል እና ባለድርሻ አካላት ጋር የኦዲት በጀት አፈጻጸም በአመያ ከተማ እየገመገመ ነዉ።

የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ የአፈጻጸም ግምገማውን በንግግር በከፈቱበት ወቅት ፣የክልሉ ኦዲት አስመላሽ ግብረሃይል አጠቃላይ 14 አባላትን ያቀፈና በክልሉ ምክር ቤት አስተባባሪነት የኦዲት ግኝት ሥራዎች እየተገመገሙ እና እየተመራ መሆኑን ገልጸዋል።

የክልሉ ኦዲት አስመላሽ ግብረሃይል በየጊዜው በሚያካሂዳቸው ስብሳባዎች እና በሚያስቀምጣቸው አቅጣጫዎች ውጤቶች እየተመዘገበ መሆኑንም ክቡር ዋና አፈ-ጉባኤው አስረድተዋል።

የፋይናንስ ሀብት አጠቃቀምና የአሠራር ሥርዓት በማስተካከል የመንግስት እና ህዝብ ሀብት ከብክነት በመታደግ ለታለመለት ዓላማ ብቻ እንዲውል መደረግ እንዳለበትም በንግግራቸው ጠቅሰዋል።

አሁንም በአንዳንድ ተቋማት ኦዲት ተደርገው ኦዲት ግኝት ባለመደረጋቸው በሚሰጡት ምላሾች ላይ የጥራት ችግር እና በታችኛው መዋቅሮች ግብረሃይል ጠንካራ ያለመሆን ችግሮች የሚታይ በመሆኑ አሁንም ግብረሃይሉ በልዩ ትኩረት እንዲመራ አስገንዝበዋል።

በፋይናንስ ሀብትና ንብረት አስተዳደር ላይ የሚታዩ የአሠራር ጥሰቶች እና የሀብት ብክነት ችግሮች ላይ ተገቢውን የእርምት እርምጃ መውሰድ፣ግልጽነት እና ተጠያቂነት ማረጋገጥ የሚያስችል ሁኔታ መፍጠር የመድረኩ ዋና ዓላማ ነዉ።

በመድረኩ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕረዚዳንት አቶ ቆጭቶ ገ/ማሪያም፣ የክልልና የዞን የፋይናንስ ኃላፊዎች፣ የዞን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤዎች ፣የክልሉ ምክርቤት ቋሚ ኮሚቴዎች፣የኦዲት አስመላሽ ግብረሃይል አባላትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ነዉ።

በፍቅር ከበደ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *