


በኮንታ ዞን አመያ ዙሪያ ወረዳ በኦፓላሸ ቀበሌ በግምት ከምሽቱ 9 ሰዓት አካባቢ በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ የሶስት ሰዎች ህይወት አልፏል ።
ሰሞኑን የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ በቀበሌው በተከሰተ የመሬት መንሸራተት አደጋ እናትን ጨምሮ ሁለት ልጆች በአደጋው ህይወታቸውን አጥተዋል።
ከሟቾች መካከል የ11ኛ ክፍል ተማሪ የሆነችው ተማሪ አግኔ አሉላ፣ ታናሽ ወንድሟና የ6ኛ ክፍል ተማሪ አማኑኤል አሉላ እና እናታቸው ወ/ሮ ዳምአሌ ደስታ ናቸው።
በደረሰው አደጋ ከሟቾች በተጨማሪ በኦፓ ላሸ እና በኮዳ ማጂ ቀበሌ 25 አባዎራዎችና 175 የቤተሰብ አባላት ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በቀበሌ ውስጥ ተጠልለው እንደሚገኙ ለማረጋገጥ ተችሏል።
በአደጋው አምስት የቤት እንስሳት መሞታቸውንና በ5 ነጥብ 5 ሄክታር ማሳ ላይ የነበረ ሰብል መውደሙም ተጠቁሟል።
ዘገባው የኮንታ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው።
