የጤና ተቋማትና ባለሙያዎች ቁጥር መጨመር በሚሰጡ አገልግሎቶች የጥራት መጓደል እንዳያስከትል ተከታታይነት ያለው የስራ ላይ ስልጠና አስፈላጊነቱ የጐላ እንደሆነ ተገለፀ።
በክልሉ አራተኛውን በህክምና ሙያ ላይ ለተሰማሩ ባለሙያዎች ተከታታይነት ያለውን ስራ ላይ ስልጠና የሚሰጥ ማዕከል በታርጫ ጠቅላላ ሆስፒታል ለመክፈት ዝግጅት እየተጠናቀቀ እንደሚገኝ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ አስታውቋል።
ከዝህ ቀደም በክልሉ የጤና ባለሙያዎች የስልጠና ማዕከል ፍቃድ አግኝተው ስልጠና በመስጠት ላይ የሚገኙት በካፋ ዞን የገብረፃዲቅ ሻዎ ሆስፒታል ፣ በቤች ሼኮ ዞን የሚዛን አማን ሆስፒታል እና ሚዛን ቲፒ ጤና ሣይንስ ኮሌጅ ናቸው።
የጤና ቢሮ ኃላፊ ተወካይና የጤናና ጤና ነክ አገልግሎት ግብአት ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣ ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን አሰፋ እንደገለጹት ባለፉት ዓመታት የታርጫ ጠቅላላ ሆስፒታል በአካባቢው ለጤና ባለሙያዎች ስልጠና(CPD) የሚሰጥ ማዕከል ያለመኖር ችግር ሆኖ ቆይቷል።
ይንን ለመቅረፍም ሆስፒታሉ በመስፈርቱ መሰረት እንዲመዘን ለጅማ ዮኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኢንስቲትዩትን በተደጋጋሚ ጥያቄ መቅረቡንም አውስተዋል።
የጤና ተቋማትና ባለሙያዎች ቁጥር እንደ ክልል እየጨምረ ከመምጣቱ ጋር የሚሰጡ አገልግሎቶች ጥራታቸው እንደይጓደል የተከታታይ ስልጠና አስፈላጊነቱ የጐላ እንደሆነ ገልፀዋል።
በመሆኑም የታርጫ ጠቅላላ ሆስፒታሉ አሁን ላይ ሥልጠና በክልሉ ውስጥ በሚገኙ የጤና ተቋማት ውስጥ ለሚሰሩ ባለሙያዎች ስልጠና ለመስጠት ተጨማሪ አማራጭ መሆኑን ከክልሉ ጤና ቢሮ ከጅማ ዩኒቨርስቲ እና ከታርጫ ጠቅላላ ሆስፒታል የተወጣጡ አካላት አረጋግጠዋል።
የታርጫ ጠቅላላ ሆስፒታል ኃላፊ አቶ ያዕቆብ ሌንጫ እንደገለጹት በአካባቢው የጤና ባለሙያዎች ተቀብሎ ስልጠና (CPD) የሚሰጥ ማዕከል ባለመኖሩ ባለሙያዎቹ ስልጠና ለመውሰድ ሲቸገሩ እንደቆዩ ተናግረው ማዕከሉ በታርጫ ጠቅላላ ሆስፒታል መከፈቱ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ይረዳል ብለዋል ሲል
የቢሮው ኮሙንኬሽን ገፅ መረጃ አድርሷል።
