በመደመር ፍልስፍና መሰረት የሰው ልጆች ነፃ ፍቃድ በየጊዜው እያደገ

Spread the love

በመደመር ፍልስፍና መሰረት የሰው ልጆች ነፃ ፍቃድ በየጊዜው እያደገ የሚሄድና በዕድገቱ ውስጥም የዕውቀትና የስነ ልቦና ኃይል እያዳበረ የሚሄድ ነው።የሰው ልጆች ጉዞም ነፃ ፍቃዳቸውን እያጠነከሩ ከአካባቢና ከተፈጥሮ ባሪያነታቸው ነፃ እየወጡ የሚመጡበት ሂደት ነው።

ስለዚህም የሰው ልጆች ነፃ ፍቃድ ቀደም ብለው በሰሩት ስራ ላይ የሚመሰረት ነው።ይህም ማለት ትናንትና የሰራቸውን ስራዎች ለቀጣይ ስራቸው መነሻ ወረት ይሆናቸዋል ማለት ነው።

ሰዎች ነፃ ፍቃድ አላቸው።ነፃ ፍቃዱ ግን ሙሉ ፈቃድ አይደለም።ተፈጥሮን እያሸነፉ በመጡ ቁጥር ነፃ ፈቃዳቸው እየጎለበተ ይመጣል።ሆኖም ይህ እየጎለበተ የመጣው ነፃ ፈቃድ ተፈጥሮን ቢያሸንፉም የራሳቸው የእጅ ስራ መልሶ ራሳቸውን የሚያሸንፋቸውና ነፃ ፈቃዳቸውን የሚወስንላቸው እየሆነ መጥቷል።

በመደመር ዕይታ መሰረት የሰው ልጅ የፉክክርም ሆነ የትብብር የጠበኝነትም ሆነ የሰላማዊነት ዝንባሌው በእጁ ላይ ነው።የሚፈልገውን ባሕርይ የመገንባትና የማጠናከር አቅም አለው።የሰው ልጅ ስልጣኔ የእያንዳንዱን ሰው ፍላጎት በማሟላት ሙሉ በሙሉ የበሰለ እውነተኛ ስልጣኔ እንዲሆን ይህን የሰው ልጆች ዐቅም መገንዘብ ግድ ይላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *