የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በወቅታዊ የግብርና ጉዳዮች ላይ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፥-
- በበልግ 2.4 ሚሊዮን ሄክታር ለመሽፈን ታቅዶ 2.7 ሚሊዮን በዘር ተሸፍኗል። 48 ሚሊዮን ኩንታል ተሰብስቧል።
- በመኸር 17.4 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ለማልማት ታቅዶ 17.5 በዘር ተሸፍኗል።
- ከዚህ ውስጥ 8.6 ሚሊዮን ሄክታር በኩታ ገጠም የለማ ሲሆን 4 ሚሊዮን ሄክታር ደግሞ በትራክተር የታረሰ ነው።
- የበርሃ አንበጣ በ5 ክልሎች አጎራባች ወረዳዎች የተከሰተ ሲሆን በተደረገው የመከላከል ስራ ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር ተችሏል።
- በስምጥ ሸለቆ አካባቢዎች የተከሰተው የግሪሳ ወፍ የኬሚካል ርጭት እየተካሄደ ነው።
- ዘንድሮ በመስኖ በ3 ሚሊዮን ሄክታር መሬት 117 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ ለማምረት እየተሰራ ይገኛል።
- ለ2015/16 የምርት ዘመን 13.9 ሚሊዮን ኩንታል ማዳበሪያ ተገዝቶ ወደ ሀገር ገብቷል።
- ለ2016/17 የምርት ዘመን ደግሞ 23 ሚሊዮን ኩንታል ማዳበሪያ ለመግዛት ታቅዶ እየተሰራ ይገኛል።
- የተንዛዛ የማዳበሪያ ግዥ ስርዓት ተሻሽሎ ሂደቱ እንዲያጥር ተደርጓል።
- ነሐሴ ላይ አስፈላጊው የማዳበሪያ ግዥ ተፈጽሟል።
- የግዥ ሂደቱን ከማሳጠር ባሻገር በማዳበሪያ ዋጋ ላይ ጥናት ተደርጎ ዝቅ ባለ ዋጋ ግዥ ተፈጽሟል።
- 2 ሚሊዮን ኩንታል ማዳበሪያ ለመስኖ ልማት ይውላል።
- 92 ሺ ሄክታር መሬት ላይ ምርጥ ዘር ብዜት ታቅዶ እስካሁን 78 ሺ ሄክታር ላይ የብዜት ስራ ተሰርቷል።
- በምርት ላይ ብክነት እንዳይከሰት ሕብረተሰቡ የደረሱ ሰብሎችን በወቅቱ መሰብሰብ ይኖርበታል።
