በክልሉ ያለው የተሟላ ሠላምና መረጋጋት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን የሚጋብዝ ነው:- ወ/ሮ ወሰነች ቶማስ

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ የሲቪል ማህበረሰብ ልማት ድርጅቶች የጋራ ፎረም ውይይት አካሄድ።

ቢሮው በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ የተለያዩ የሲቪል ልማት ድርጅቶችና ባለድርሻ አካላት ጋር በሀላላ ኬላ ሪዞርት የአንድ ቀን ውይይት አድርጓል።

በጋራ ጉባኤው በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የሲቪል ማህበረሰብ ልማት ድርጅቶች አጠቃላይ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቧል።

በክልሉ 40 የሲቪል ማህበረሰብ የልማት ድርጅቶች 71 የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ከ3.9 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ፌንድ እየተገበሩ መሆኑ ተጠቁሟል።

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በገቡት ውል መሠረት ተግባራትን እየፈጸሙ ስለመሆናቸው የመከታተልና መቆጣጠር ስራ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ነወ የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ወሰነች ቶማስ የገለፁት።

የልማት ድርጅቶቹ በክልሉ በመንግሥት ያልተሸፈኑ የልማትና ደህነት ቅነሳ መስኮች ላይ በርካታ ተግባራት እያከናወኑ መሆኑን የገለጹት ኃላፊዋ ካለው የልማት ፍላጎት አኳያ ቁጥራቸው አናሳ መሆኑን አንስተዋል።

በክልሉ ያለው የተሟላ ሠላምና መረጋጋት ምቹ በመሆኑ ሌሎች የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ወደ ክልሉ በመምጣት የሕብረተሰቡን የልማት ክፍተቶች ለመሙላት እንዲሳተፉ ወ/ሮ ወሰነች ጥሪ አቅርበዋል ።

የክልሉን ህዝብ አንገብጋቢ የልማት ጥያቄዎችን ለመሙላት መንግሥት እያደረገ ያለውን ጥረት በመደገፍ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሚና የጎላ መሆኑን የገለጹት የክልሉ ረዳት የመንግሥት ተጠሪ አቶ በላይ ተሰማ ተግባሩ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

በልማት ድርጅቶቹ እየተሰሩ ያሉ የልማትና የደህነት ቅነሳ ስራዎች የህዝቡን ችግር የፈታ መሆኑን በተጨባጭ ማረጋገጥ እንደሚገባ አቶ በላይ ተናግረዋል።

ተጨማሪ ሀብት በማሰባሰብና ሌሎች የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ወደ አከባቢው በመጋበዝ የተለያዩ የልማት ክፍተቶችን ለመሸፈን ጥረት መደረግ እንዳለበትም አስገንዝበዋል።

በጋራ ፎረሙ በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አጠቃላይ አሰራር እንዲሁም የተመረጡ የልማት ድርጅቶች አፈጻጸም ስነድ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በክልሉ ያለው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ቁጥር አናሳ በመሆኑ የስርጭት ፍትሀዊነት ማረጋገጥ ያልተቻለ መሆኑን አንስተዋል።

የክልልና የዞን የሥራ ኃላፊዎች፣ የፕሮጀክት አስተባባሪዎች፣ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በጋራ የሚሰሩ ተቋማት አመራርና ባለሙያዎች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተሳተፉበት በዚህ መድረክ የባለአምስት ነጥብ የጋራ አቋም መግለጫ በማውጣት መድረኩ ተጠናቋል ።

ዕድገቱ በዛብህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *