




በክልሉ በትምህርት ዘርፍ ስራዎች በተደረገ የድጋፍና ክትትል ስራ የግብረ መልስ መድረክ ተካሂዷል።
የክልሉ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች በዳውሮ፣ በኮንታ፣ በቤንች ሸኮና በካፋ ዞን በ16 ትምህርት ቤቶች ያደረጉትን የድጋፍና ክትትል ስራዎች ሪፖርት በዝርዝር አቅርበዋል።
የግብረ መልስ መድረኩን የመሩት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ዋና አፌ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ በምክር ቤቱ ቀሚ ኮሚቴዎች በትምህርት ዘርፍ የሚደረጉ የድጋፋዊ ክትትል ስራዎች ለዘርፉ ውጤታማነት ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳለው ጠቁመዋል።
በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ አልማው ዘውዴ በበኩላቸው በክልሉ በትምህርት ዘርፍ ባለፈው ጊዜያት በተሰሩ ስራዎች ለውጥ እየታየ ቢሆንም የሚፈለገውን ውጤት ለማምጣት የተጀመሩ ርብርቦችንና ቅንጅታዊ አሰራሮችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ የቢሮው ሀላፊ ገልፀዋል።
አቶ አልማው አክለውም የድጋፋዊ ክትትል ስራ ትልቅ አቅም የሚፈጥር ስለሆነ የተነሱ ጉዳዮችን ወስዶ መስራት ከሁሉም የሚጠበቅ ሀላፊነት እንደሆነም አብራርተዋል።
ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መስራት የትምህርት ዘርፍ ስራ ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆን ያስችላልም ብለዋል።
አመራሩ የትምህርት ዘርፍ ጉዳይን የፊት አጀንዳ አድርጎ መንቀሳቀስ ይገባልም ብለዋል።
አቶ አልማው ምክር ቤቱ በቀጣይነት መደገፍ የሚገባቸውን ጉዳዮች በዝርዝር ያቀረቡ ሲሆን በቀጣይ በመልካም የተነሱትን ለማጠናከርና በጉድለት የተነሱትን ለማረም በልዩ ትኩረት ይሰራልም ብለዋል።
የክልሉ ምክር ቤት ምክትል አፌ ጉባኤ ወ/ሮ ፀሀይ ዳርጫ የትምህርት ስብራትን በመጠገን የማህበራዊ ብልፅግና ለማረጋገጥና ጠንካራ ትውልድ ለመፍጠር ምክር ቤቱ በትኩረት ይሰራል ብለዋል።
የድጋፍና ክትትል ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የገለፁ ምክትል አፌ ጉባኤዋ በተለይ በግብረ መልሱ ወደ ኋላ በመቅረት የተገመገሙ ዞኖች በልዩ ሁኔታ መደገፍና የተጠያቂነት አሰራር በመዘርጋት መስራት እንደሚያስፈልግ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
የትምህርት ቢሮ ምክትል ሀላፊዎች የምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች ያደረጉትን የድጋፋዊ ክትትል ስራ ለትምህርት ውጤታማነት አጋዥ መሆኑን አንስተው እንደ ማነቆ የተነሱ ጉዳዮችን በቀጣይ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ አስረድተዋል።
ከምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴዎች የተሰጡ ግብረ መልሶችን ተቀብሎ መስራት ያስፈልጋል ያሉት የቢሮው ማኔጅመንት አባላት ድጋፋዊ ክትትሉ ተጠናክሮ ልቀጥል እንደሚገባ ጠይቀዋል።
