



በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ካፋ ፣ ዳውሮ ፣ቤንች ሸኮ፣ኮንታ እና በምዕራብ ኦሞ ዞኖች ”የመሐሉን ዘመን ወጥመድ መሻገር” በሚል ርዕስ ዞናዊ የአመራር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
መድረኮቹ በቦንጋ፣ ሚዛን አማን፣ታርጫ፣አመያ እና በጀሙ ከተሞች እየተካሄደ የሚገኝ ሲሆን በዚህም መሐሉን ዘመን ወጥመድ መሻገር” በሚል ርዕሰ ላይ ውይይት እየተደረገ ነዉ።
በመድረኮቹም፤የለውጥ መንግስት ባለፉት የለውጥ አመታት በፈተናዎች የታጀበ ቢሆንም ሁለንተናዊ ብልፅግና እያረጋገጡ ያሉ ስኬቶች በዞኖች፣ በክልሉ ብሎም በሀገሪ ደረጃ አመርቂ ውጤቶች እየተመዘገቡ መሆናቸውም ተገልጿል።
የመሀሉ ዘመን ወጥመድን በመሻገር እየተመዘገበ ያለዉ ለውጥ እንዲቀጥል የአመራሩ ብቃት፣ ቁርጠኝነትና የህዝብ አገልጋይነት ከመቼውም ጊዜ በላይ እንዲጠናከር ተጠይቋል።
ለውጡን ወደ ተሟላ ወጤት ለመቀየር የተፈጠረውን አንጻራዊ ሠላምና አስተማማኝ ህልውና፣ ኢኮኖሚያዊ መሠረትና መደላድል እንዲሁም ውስጣዊና ውጫዊ አስቻይ ሁኔታዎችን በአግባቡ በመጠቀም ወደ ቀጣዩ ምዕራፍ መሸጋገር እንደሚገባም ተነስቷል።
በመድረኩ የዞኑ፣ የወረዳ እና የከተማ አስተዳደር አስተባባሪ አካላት፣ የዞን መዋቅር አጠቃላይ አመራሮች በመሳተፍ ላይ መሆናቸውን የዞኖች መረጃ ያመላክታል።
በፍቅር ከበደ
