




በቤንች ሸኮ ዞን “የሚዲያና ኮምንኬሽን ሚና ለሁለንተናዊ ብልጽግና” በሚል መሪ ቃል በዞኑ የሚገኙ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን አመራሮችና ባለሙያዎች የሚሳተፉበት መድረክ እየተካሄደ ነው።
የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ ካፍትን መድረኩን በንግግር ሲከፍቱ እንደተናገሩት የአንድ ሀገር ሁለንተናዊ ልማትና ዕድገት ግለቱን ጠብቆ እንዲቀጥል የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች ሚና የጎላ ነው ብለዋል።
በሀገር እና ሀገረ መንግስት ግንባታ ሂደት ውስጥ ገዥ ትርክትን በማስረጽ ፣ ዜጎች ሚዛናዊና ምክንያታዊ ተግባቦትን እንዲያጎለብቱ የዘርፉ ሚና ከፍተኛ ነው ሲሉ ጠቁመዋል።
የኢትዮጵያ መንሰራራት እውን እንዲሆን ፤ ለሀገር ሉአላዊነትና ለጋራ ተነሳሽነት ፤ ለዲምክራሲያዊ ስርዓት ግንባታና ሰላምን በማፅናት ረገድ የሚዲያና ኮምንኬሽን ባለሙያዎች የተጣለባቸውን ብሔራዊ ኃላፊነት በአግባቡ ሊወጡና አሻራቸውን ሊያሳርፉ ይገባል ብለዋል።
መድረኩ ቀጥሎ እየተካሄደ ሲሆን የዞኑ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሙባረክ አበበ በመድረኩ የመወያያ ሰነድ እያቀረቡ ይገኛሉ።
በመድረኩ ከዞኑና ከወረዳ የመንግስት ኮምንኬሽን አመራሮችና ባለሙያዎች ፣ ከደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የሚዛን ኤፍ ኤም 104.5 ቅርንጫፍ ፣ የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን የሚዛን አማን ፋና ኤፍ ኤም 92.5 ጣቢያ አመራሮችና የሚዲያ ባለሙያዎች እየተሳተፉ መሆናቸዉን የቤንች ሸኮ ዞን የመንግሰት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት መረጃ ያመለክታል።
