






የዞኑ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ከበደ ሲሳይ እንደገለጹት የተሻለ የሕዝብ ግንኙነት ሥራና አገልግሎት በተጨባጭ መረጃ በማደራጀት ለኅብረተሰቡ ማድረስ እንዲቻል የሚያግዙ ተግባራት ለሚዲያ አመራሮችና ባለሙያዎች እየተከናወኑ ይገኛል ።
ከዚህ የተነሣ በየደረጃው ለሚገኙ በዳውሮ ዞን ለሚገኙ የሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን አመራሮችና ሠራተኞች ሥልጠና ተዘጋጅቷል።
በሥልጠናው አገራዊ፣ ክልላዊና ዞናዊ የማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ የልማት ሥራዎችና የተመዘገቡ ድሎችን በማስተዋወቅ በኩል ለዘርፉ አመራሮችና ባለሙያዎች የጋራ ግንዛቤ ለመፍጠር እንደሚያግዝም ገልጸዋል።
የዞኑ የመንግሥት ዋና ተጠሪና አቶ ታሪኩ አካሉ በበኩላቸው የሚዲያ ተቋማት አገራዊ የብልጽግና ጉዞን ለማረጋገጥ በሚደረገው ሂደት አፍራሽ ተልዕኮን ለመመከት እንዲቻል የተጣለባቸው ሕዝባዊና መንግሥታዊ ተልዕኮን በመረዳት ተግባራቸውን ነጻና ገለልተኛ በሆነ መንገድ ማከናወን እንደሚገባቸው ገልጸዋል።
አሁን ላይ የሚዲያ ባለሙያዎች ለገዥ ትርክትና ሀገረ መንግሥት ግንባታ ላይ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ላቅ ያለ በመሆኑ በውጤት የታጀበ ተግባራት ላይ የድርሻቸውን እንዲወጡም ጠይቀዋል።
