በቤንች ሸኮ ዞን የሚገኙ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች በፌደራል መንግስት እየተገነቡ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን ጎበኙ።

Spread the love

“የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሚና ለሁለንተናዊ ብልጽግና በሚል መሪ ቃል” በሚካሄደው መድረክ የሚሳተፉ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች በፌደራል መንግስት እየተገነቡ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

በቤንች ሸኮ ዞን የሚገኙ የሚዲያና ኮምንኬሽን ባለሙያዎች “የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሚና ለሁለንተናዊ ብልጽግና” በሚል መሪ ቃል በዞኑ የሚገኙ አጠቃላይ የሚዲያና ኮምንኬሽን ባለሙያዎች መድረክ በሚዛን አማን እየተካሄደ ይገኛል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች በጠዋቱ ፕሮግራም በፌደራል መንግስት እየተገነቡ የሚገኙ የገበታ ለትውልድ አካል የሆነውን የደንቢ ሎጅና የሚዛን አማን አውሮፕላን ማረፊያን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ የደንቢ ሎጅ አጠቃላይ የግንባታ ስራው በፍጥነት እየተከናወነ ሲሆን አፈፃፀሙም 96.5 በመቶ መድረሱ ተገልጿል። በቅርቡም የግንባታ ስራው ተጠናቆ ለምረቃ ዝግጁ እንደሚደረግም በገለጻው ተጠቁሟል። ግንባታውን የሚድድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ እያከናወነ መሆኑም ተጠቁሟል።

ሰኔ 2013 በጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) የመሰረተ ድንጋይ ተጥሎ ወደ ስራ የገባው የሚዛን አማን አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ዛሬ ላይ የአስፓልት ማንጠፍ ስራ እየተሰራ መሆኑ በኮምንኬሽን ሚዲያ አካላት ተጎብኝቷል። የግንባታው አፈጻጸም 78 በመቶ የደረሰ ሲሆን ግንባታውን በፍጥነት ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑ በገለጻ ወቅት ተጠቁሟል።

በጉብኝቱ የተሳተፉ የሚዲያና ኮምንኬሽን አመራርና ባለሙያዎች እንደተናገሩት ፕሮጀክቶቹ ለዞኑ ትልቅ ገፀ በረከቶች መሆናቸውን ገልጸዋል። ፕሮጀክቶቹ ተጠናቀው ወደ ስራ ሲገቡ በዞኑና በአጎራባች አካባቢዎች የንግድ ፣ የኢንቨስትመንትና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን እንደሚያጠናክር ገልጸዋል።

በጉብኝቱ በመሳተፋቸውን ደስተኛ መሆናቸውን የገለጹት ባለሙያዎቹ እንደዚህ አይነት የጉብኝትና ሀገርን የማወቅ ተግባራት ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ ማንሳታቸዉን የቤንች ሸኮ ዞን የመንግሰት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ነዉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *