የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ በመንግስትና ህብረተሰብ ተሳትፎ የሚከናወኑ ተግባራት ለማስተዋወቅ ያላቸው ሚና ከፍተኛ ነው።

Spread the love

‎በክልል፣ በዞንና፣ በወረዳ በከተማ አስተዳደር የሚገኙ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን አመራሮችና ባለሙያዎች በዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎችን ጉበኙ።

‎የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ተቋማት አመራሮችና ባለሙያዎች በከተማ አስተዳደሩ በተደራጁ ወጣቶች እየተሰራ የሚገኝ የዶሮ እርባታ ማዕከል፣ የከተማ ግብርና ስራዎችንና የከተማ ኮሪደር ልማት ስራዎችን ተዟዙረው ጎብኝተዋል

‎በጉብኝቱ የተገኙ የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ መንግስቱ መኩሪያ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ በመንግስትና ህብረተሰብ ተሳትፎ የሚከናወኑ ተግባራት ለማስተዋወቅ ያላቸው ሚና ከፍተኛ መሆኑን አስረድተዋል።

‎ተቋማቱ ጠንካራ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ተግባር በማከናወን በአገር ግንባታ ላይ ያላቸውን ሚና መወጣት ልወጡ ይገባልም ብለዋል።

‎መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገ መሆኑን የገለፁ የተደራጁ ወጣቶች በተለይ ስራ አጣን የሚሉ ዜጎች የስራ ባህልንና አመለካከትን በመቀየር በየትኛውም የስራ ዘርፍ በመሰማራት ውጤታማ መሆን እንደሚቻል አስረድተዋል።

‎በከተማ አስተዳደሩ እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎች ተስፋ ሰጪ መሆኑን የገለፁ የጉብኝቱ ተሳታፊ የሚዲያ ባለሙያዎች በመንግስትና በህብረተሰብ ተሳትፎ የሚከናወኑ ተግባራትን የማስተዋወቁን ስራ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።

‎የሚዲያ ተቋማትና ባለሙያዎች አሰባሳቢ ትርክቶች የበላይነት እንዲይዙ ከማስቻልም ባለፈ በአገር አንድነትና ሰላም ላይ ያላቸውን ከፍተኛ ሚና በአግባቡ ለመወጣት በቅንጅት ልሰሩ እንደሚገባም ተብራርቷል።

‎በጉብኝቱ የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ ሀላፊዎችና አጠቃላይ ሰራተኞች፣ የዳውሮ ዞን ፣ የወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የመንግስት ኮሙኒኬሽን የስራ ሀላፊዎችና ባለሙያዎች እንዲሁም ሌሎች የባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *