




በካፋ፣ ሸካ እና በቤንች ሸኮ ዞኖች የብልጽግና ፓርቲ የወጣቶች ክንፍ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ” ሀገሬን እገነባለሁ ኃላፊነቴን እወጣለሁ ” በሚል መሪ ቃል ዞን አቀፍ የወጣቶች ውይይት ተካሂዷል።
መድረኮቹ ወጣቶች በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚና በፖለቲካ ሁኔታዎች ላይ ግልፅ ግንዛቤ እና የጋራ አረዳድ በመፍጠር የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ ዓላማ ያደረገ ነው።
ሀገራዊ ለውጡ እንደ ሁሉም የሀገራችን የህብረተሰብ ክፍሎች ወጣቶችን ተጠቃሚ ያደረጉ ትሩፋቶችን ያስገኘ ሲሆን፣ በተለየ መልኩም የወጣቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት የሚያሳድጉና በትውልዱ ውስጥ ያላቸውን ሚና በብቃት ለመወጣት የሚችሉባቸውን ዕድሎች ይዞ የመጣ መሆኑ በመድረኩ ተብራርቷል ።
በኢትዮጵያ የዘመናት ታሪክ ውስጥ የወጣቶች ሚና ከፍተኛ ከመሆኑም ባሻገር ሀገራችን ኢትዮጵያ በየወቅቱ የተጋረጠባትን ፈተና በድል እንዲትወጣ ጉልህ አስተዋጾ በማበርከትና ሀገር እንድትቀጥል በማስቻል ታሪካዊ ባለውለታዎች መሆናቸውን ተመልክቷል ፡፡
ወጣቱ በእውቀት አዳዲስ ሃሳቦችን በማመንጨትና የነቃ ተሳትፎ በማድረግ እንዲሁም በሀገር ግንባታ ላይ ወንድማማችነትን በማስቀደምና ህብረ ብሄራዊ ሀገር የመገንባት እንደሚገባም አጽንኦት ተሰጥቶታል ።
የክልሉን ሁለንተናዊ ልማትና ሠላምን ለማረጋገጥ ወጣቶች በፖለቲካዊ፣ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዘርፎች በመሳተፍ እያደረጉ ያሉት ተግባር መኖራቸውን የተነሳ ሲሆን በመንግሥት የተጀመሩ የልማትና የመልካም አስተዳዳር ስራዎችን በመደገፍ የጋራ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ እንዳለባቸው ተገልጿል።
አዎንታዊ ሠላም እንዲሰርጽ እንዲሁም የተረጋጋና የፀና ሠላም እንዲኖር ወጣቱ ወጣቶች በሀገር እና ሀገረ-መንግስት ግንባታ እንዲሁም በሠላም እሴት ግንባታ ላይ እያበረከተ ያለውን ሁለንተናዊ ተሳትፎ አጠናክሮ ማስቀጠል እንዳለበት በመድረኮቹ ተነስቷል።
በውይይቱ ላይ የተሳተፉ አካላት በሰጡት አስተያየት በዞኖቹ የተሰራው ስራ አበረታች ውጤቶች እየተመዘገበ በመሆኑ ይህንን አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ብለው ወጣቱ ዘንድ የቴክኖሎጂና የሚዲያ አጠቃቀም ያሉ ሂዴቶች ሀገርን በሚገነቡና አንድነትን በሚያጠናክሩ ተግባራት ላይ ትኩረት መደረግ እንዳለበትም ጠቅሰዋል።
ወጣቶች ጉልበታቸውን እና የፈጠራ አስተሳሰባቸውን ለሀገር ልማት፣ለሰላም ግንባታ እና ለማህበራዊ እድገት ሊጠቀሙ እንደሚገባ አንስተዋል።
በመድረኮቹ ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊዎች በኩል ሰነድ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።
በመድረኩም የሚመለከታቸው የክልል የስራ ኃላፊዎች ዞን ዋና ኃላፊዎችና አመራሮች ከየዞኖቹና ወረዳ እንዲሁም ከተማ አስተዳደር ወጣቶች ክንፍ አስተባባሪዎች ተገኝተዋል።
በተከተል ወ/ሚካኤል
